ቤባንያ ገፅ ፬

December 16, 2023

ለአንድ ሳምንት ያህል ሻይ በዳቦ፤ ወተት በዳቦ፤ ለስላሳ በዳቦ እየበሳላን ቆየን። አንድ ምሽት ደጃፋችን ተቆፈቆፈ፣ ጋሽ ይማም እንሶስላ የተሞቀች የምታምር ሴት አልፋው ወደ ውስጥ ዘለቀች፡፡ ጋሽ ይማም፡- “አንቺን ደሞ ላኩ? ይሁን!” አለ።በእንግድነት አልተቀመጠችም፡፡ _ ወዲያው ወደጓዳ ገብታ እያንጎዳጎደች ያለና የሌለ የሴት ዕቃ ቆጠረች:: እሳት አያይዛ የምንበላው ቀቀለች።“አብረኸት ነው ስሜ፣ አደዬ በለኝ” አለችኝ። በቀጣዩ ቀን · የቤቱን አውድ ቀየረች:: አዲስ መጋረጃ አምጥታ ጋሽ ይማም የሚቅምበትን ቦታ ጋረደች:: በጫት ሰዓት ተከናንባ ቡና ታፈላለች:: ጫት ሲሰጣት ተነስታ ስማ ትቀበላለች:: ጋሽ ይማም ይዘይራል፡፡”አሜን፤ አሜን! አሜን! አሜን!እኔን ከፋኝ እንጂ አገሬን ምን ከፋው?አበቀለ ግራር ዝሆን የማይገፋው።አሜን፤ አሜን!አገሬ ላይ ሆኜ ናፈቀኝ አገሬ፣ከማን ጋር ይኖራል ሁሉም ሆኗል አውሬ፣”ሳይታሰብ ቤቱ ሰው ይሞላል:: ጫማውን አውልቆ የሚገባ ይበዛል:: ጋሽ ይማም ሲዘይር እ-ህ-ህ-ህ-ህ የሚል አጃቢ ጨመረ ከንፈሩን የሚመጥም አለ፡፡ እንዲህ እየደጋገምን ብዙ ቆየን፤አንድ ቀን ምሽት ላይ ከረሜላ በኮት ኪሱ ይዞ መጥቶ እየሰጠኝ፡-“ልጁ፣ ከረሜላ ምጠጥ” አለኝ።አጠገቡ ተቀምጬ ማሸጊያውን መፈታታት ጀመርኩ:: እንግዲህ ዛሬ ምሽቱን ድምጥ ሳላሰማ እብስ ልል ነዉ አለኝ።”ወዴት?””እንጃ ደሞ ወዳንዱ፣ ሂድ ሂድ ሂድ የሚሉን አሉብን“እኔም አብሬህ እሄዳለሁ”እንዳልሰማ ሆኖ ዘየረ “አቤ-ት፣ አቤት! አጀብ፤ አጀብ… ጌትዬ ኮምቦልሻን ለአጋይ ጤፍ ዋድላን ለባቄላ ደሞ ወዲህ ሽምብራ… ሰማዩን መሬቱን እንዲህ ስትስራ ማኖር ቸገረህ ወይ ከምንወደው ጋራ አጀብ፤ አጀብ”እኔም እሄዳለሁ… አልኩ ደግሜ“ምን በወጣህ በረሃ ለበረሃ የምትንከራተተው? እዚሁ ከጥላው አረፍ በል:: እኛ ሲመቸን የማይወዱልን ናቸው የሚያንቀዠቅዡን፡፡ ምን እንዳዘጋጁልንም እንጃ…”ማታ ብትሩን ጫንቃው ላይ አጋድሞ ወጣ። “ናፈቀኝ ናፈቀኝ ናፈቀኝ ሀገሬ .የተወለድኩበት ናፈቀኝ ሀገሬጎራው ሸንተረሩ ናፈቀኝ ሀገሬ ጎራው ሽንተረሩ፣ ፍየልና በጉ፣ ደጉ ሳይቀር ክፉ ሰዎች አለቁ አሉኝ እንደምነው ዛፉ፡ አሜን! አ-ሜ-ን!” ድምፁ እየተጭለመለመ ሄደ እኔን በሰው ሀገር ሀገሬን ለሌላ፣ ከሰው የበለጠ እንጀራ ላልበላ አጀብ ጌትዬዋ…..ጌ ት ዬ ዋ!!ሳለቅስ አብረኸት እንደ አንድ ክፉ ድርጊት አይታ ተትከነከነች:: ከንዴቷ የተነሳ ሹሩባዋ እየተፈታ ፀጉሯ ቆመ፤ የጠራ አማርኛ መናገር ተሳናት፡፡”ሱቅ በል! ባለጌ ልጅ! እኔን የሚያስወቅስ አንተ ሰዲዱለይዶ? ምንድነው የወረደብኝ? አታመን እዩ ረንሙኒ ነይሩን (ማን ረግሞን ነበር እዋይ!) እቶም ወለደይል ክመርቅኒ እኳ ዝነበሩ (ወላጆቼ ግን ሲመርቁኝ ነበር) አውቅልሃለሁ።” እኔን የሚያስወቅስ _ የማደርገውንስ _ ነአካለበችኝ ያጠፋሁት ግራ እስኪገባኝ ድረስ ቁጣዋ ገዘፈ፡፡”አደዬ…” ስላት“አደይ አትበለኒ አዴኻ ድለ” (እናቴ አትበለኝ እናትህን ፈልን ባለገይ!ጋሽ ይማም ሽመሉን ከጫንቃው ላይ ሳያወርድ በበረሃ ግልብልቢት መካከል እየተንጨለጨለ እብስ ሲል ለረጅም ጊዜ ይታየኛል:: ማናቸው፣ ከተወደደበት ጥላ ስር ነቅለው እዚያ በረሃ- ለበረሃ እንዲንከራተት የፈረዱበት?ጋሽ ይማምን ትቼ አብረኸትን መለማመጥ እንደሚሻለኝ ወሰንኩ። ከጓዳ ወደ ሳሎን፣ ከሳሎን ወደ ጓዳ መመላለስ ዋነኛ ሥራዋ ነው:: የምትሰራውን ይዛ አንድ ቦታ አትቀመጥም፡፡ ጓዳ ድስት ትጥድና ሳሎን ድንች ትልጣለች ሸተተ?” ትልና በፍጥነት ወደጓዳ። አማስላ ስትጨርስ ወደ ሳሎን…ደስ ስትሰኝብኝ እናትነቷን አይኖቿ ሲያበሩና በፈገግታዋ በኩል አሙልቃ አየዋለሁ።ፈገግ ትልና“ዕቡቅ ዝወደይ! ፅቡቅ ሪኣ!” (ጥሩ የኔ ልጅ! ጥሩ አየሁ!)…እኔም የምታወራልኝ ተረት ይሁን ታሪክ ስለሚጥም አብሬአት እንጦለጦላለሁ።የኛ ሃገርማ ሁሉ ንፁህ ነው:: ውለታ አይረሱም። እርግጥ ቂምም አይረሳም::” ከፀጉር የቀጠነ ሹሩባዋ መካከል በሹል ጥፍሮቿ ቆፈር ቆፈር አድርጋ:: አፍንጫዋን ወደ ጓዳ ትቀስራለች:: ተነስታ ወደጓዳ… እከተላለሁ፡፡

“አወሪልኛ አደዬ” እላለሁ።”ውረ-ኛ ትላለች ፈገግ ብላ::”ውለታ አይረሱም አላልኩህም? አንድ ጊዜ’ በድሮ ጊዜ የአሜሪካው ንጉስ ተገደሉ አሉ፡፡ እዛ ትግራይ ድረስ ዘይቱን፣ ብስኩቱን፣ ወተቱን…. እየላኩ በችግር ጊዜ ውለታ ውለዋል። እ-ው ይ፣ እ-ወ-ይ! ተባለ። ምግብ ለሥራ እያሉ ለራሳችን በሰራን የሚያበሉን ሰው ሞቱ! እየተባባሉ ተጠራሩ:: ሥማቸው ኬኔዲ ነው አሉ:: የአጎበር ቀብር አዘጋጀ ገበሬው::”የአጎበር ቀብር ምንድነው?”ወጡን አማስላ ውሃ ጠብ ካረገች በኋላ ወደሳሎን ጉዞ አደረግን።”የአጎበር ቀብርማ፤ ሌላ ቦታ ከተቀበረ የቆየ ወዳጅ ወይም ዘመድ ካለ’ ልክ አስከሬነ እንዳለ ተደርጎ የተሸፋፈነ ሳጥን፤ ወይም በእንጨት አራት ማዕዘን ያለ ነገር ይሰራና እንደሬሳ ታጅቦ እየተለቀሰ ቀብር ቦታ ይወሰዳል። በአስከሬን ደንብ ሳጥኑ ይቀበራል::””እሺ” ድንች እየላጠች,,,,,”እናቴ ስትነግረኝማ የኬኔዲ ቀብር ከባድ ነበር። እንዲህ እየተባለ ተገጠመ::ግኬኔዲ’ ኬኔዲ’ ኬኔዲእታ-ዞም አማሪካ`ስ ዓቢዶም ግዴ?! ንጉሶም ይቀትሉ አብ ማእኸል መንገዲ መፂ እና ኸይንቋብር ርሒቁ መንገዲ ፅንዐቱ ይህቦም ን ወለዲምን ማለት ነው? እሷም እንባዋ የመጣ መስለኝ።”ቋንቋ ተማር እሺ?… ቶሎ ብለህን…” “እሺ” እየተቁነጠነጥኩ። ኬኔዲ’ ኬኔዲ’ ኬኔዲ አሜሪካኖቹ አበዱ ወይ? ንጉሳቸውን በአደባባይ የገደሉት ስቀበርሀ ለመምጣት መንገድ እራቀብን። ነው ያሉት…..” ከንፈሯን በህዘን መጠጠች፡፡ “እዋይ ዘመዶች! እዋይ ዘመዶቼ ! አደራ እያጎድሉዎቹ! ውለታ አይረሱዎቼ! እዋይ ዘመዶቼ!! በናፍቆት ልታለቅስ ሲሆን… ያሉ“…አብረኸት!” እላታለሁ “አንተ ባለገይ ለኔ ልታሰድበኝ አብረኸትአልከኝ? እ-ዋ-ይ! እዋይ!!“አሁንማ አበላሽተኸዋል እ-ዋ-ይ!”ከአመት በኋላ ይመስለኛል አንድ ጠዋት ከእንቅልፍ ነቅተን ደጃፍ ስንከፍት ግቢያችን ተጓዥ በመሰሉ ሰዎችና አህዮች ተሞልቷል:: አደዬ ከኔ ኋላ መጥታ ያለመደነቅ አየችና ወደጓዳ ተመለሰች:: የተጓዦቹ አለቃ የመሰለ ወፈር ያ ሰው ከሁሉም ተነጥሉ የደጃፉን ግራ ይዞ ምርኩዙን ተደግፎ ተቀምጧል፡፡ አቧራ የቀላቀለ . አውሎ ነፋስ የመሰለ ብሉኮ ተከሻው ላይ ከምሯል። ደጃፍ መከፈቱን እንዳወቀ ምርኩዙን ተጭኖ ተነሳና”ቤት ለእንቦሳ፣ የቤቱ ልጆች ይደጉ፣ የትዳሩ ይዞታ ይስፋ፣ የአካባቢ አውራ ከዚህ ቤት ይውጣ!” አለኝ:: መልስ ሳይጠብቁ ወደ ሰባቶቹ ተጓዦች አተኩሮ።“ጭነቱን አውርዱ፤ የሚገባውን አስገቡ’ ደጃፍ የሚቀረውንም እራግፉ…” አለ፡፡እህል፣ ማር በስልቻ’ ቅቤ፤ ቋንጣ፤ ጭኮ… ሽታው የአካባቢውን ጠረን ለወጠው፡፡አደዬ ወደቤት የገባውን አደላድላ’ ወጣች::“ዴማ ካራ ገባብሳ ብላ’ ካአ…””ምን አልካቸው?” አለች አደዬ፡፡ በሉ መንገድ አጋምሳችሁ እደሩ፣ ተነሱ::”“አይ : ያንተ ነገር! እህል በአፋቸው ሳይዞር?… በሉ በያላችሁበት ቁጭ በሉ” ብላ ወደ ቤት ስትገባ እንግዳው ከክርኗ ከፍ ብሎ ያዛት’ እሷ ቀድማው ወቀሰች።“…እወይ፣ ሴት ያለበት የሌላ ሴት ሙያ ይዘህ ትመጣለህ? እህሉ፣ ቅቤው፣ ማሩ – ይሁን፣ ጭኮውና ድፍድፉ የምንድነው?… ብላ አንዳንዱን ስልቻ እየፈታች እየች፡፡ ትንሽ የብረት ባልዲ አምጥታ ከድፍድፉ በመቀነስ በውኃ በጥብጣ ጠላው እስኪጠራ አፋችሁ ላይ አድርጉ” የሚል ትዕዛዝ አስተላለፈች።የተጓዞቹ አለቃ ተስፋ በቆረጠ አኳኋን የነበረበት ተቀምጦ የምርኩዙን እግር ይመለከት ጀመር።አደዬ ያለስስት የጭኮውን ስልቻ በዘበዘች። አነስተኛ ሳህኖቹን እያስገባች አፍሳ ለአንድ ሰው ትሰጣለች። በመጨረሻ ለእኔም ደረሰኝ። ሥነ-ሥርዓቱ ግራ ያጋባቸው የሽኖ ሰዎች ሲመጡ እንዲገቡ እየጋበዘች ለእነሱም ጠበል ጣዲቁ እንዲደርሳቸው አደረገች። ስለቸኮለችበት ይመስላል ጠላው ባይጠራም በኩባያ እየደነበቀች በብርጭቆ አከፋፈለች:: ሥርዓት ያጣውን የድንገቴ ግብዣ የተጓዝ አለቃ በትዝብት ይከታተላል።

በአደዬ እልህ የተቀላቀለበት ግብዣ ታዳሚ ሁሉ ደስ እያለው እያመሰገነ በኋላም አደዬ አህዮቹ ምንም ሳይቀምሱ የተጫኑትን አራግፈው ብቻ መሄዳቸው ቆጭቷት ትግርኛ ባደናቀፈው አማርኛ ተብከነከነች::እውይ! ሐሳስ! አሀዮቹ፤ የእግዜር ፍጡሮች አይደሉም ወይ? እኔ ብረሳ፣ እናንተም ትረሱ?… እ-ው-ይ!”አባ ገልገሎ በዚህ አይነት ኑሯችንን ተቀላቀለ። ሰው በልቶ የጠገበ አይመስለውም:: በየወሩም በየሁለት ወሩም ከአገሩ የሚላክለት ጭነት ይራገፋል፡፡“ኢጆል! ፋአ ሂካ’ ጋርማና ገልቻ፡፡ ከሀፉ ምደሳ ለኪሳ ዋአይ ዲሮ ዱዲ ናቃባም ሮልጆች! ጭነቶቹን አራግፉ፤ ወደ ቤት የሚገባውን አስገቡ እዚህ እደጅ የሚቀመጠውን ጥግ አሲዛችሁ ደርድሩ) ይላል::ሁሌም ስለሚያመሽ ገና የአጥር በር እንዳለፈ:: ጃርቲን ኢንዲርቱ? አዶሲን ጂርቱማኒ አካን ቀባናዬ?”(አሮጊቷ የለችም? እሷ እያለች ነው ቤት እንዲህ የቀዘቀዘ?) ወደ ቤት ሳይሆን፤ የደለደለው ንጣፍ ድንጋይ ላይ ይቀመጣል፡፡አአአ… ወገቤ ተይዟል እናንተ!!… “ሜዋን ዱዲ ዋልት ቀቡ ናዲኤሳ”(እስኪ ወገብ የሚጠግን ነገር ወዲህ በይ!)እኔን “ጃተኒ” እያለ ይጠራኛል:: የእኔ እየከነከነ ሳለ አዳዬን “ሳፎይ” እያለ መጥራት ጀመረ።የእኔ ሥም`ኮ መፍትሔ ነው:: ለምንድነው ‘ጃተኒ’ ብለህ የምትጠራኝ?”በኛ በቦረኖች ቤት ሲቀየር የተወለደ ልጅ ጃተኒ ይባላል:: እኔ መች ተወለድኩ?””ለእኔ እንደተወለድክ ነው፣ ጃተኒ”መልስ እንዳገኘሁ ባይሰማኝም የአደዬን የስም ለውጥም ደርቤ ጠየኩት፡፡በኛ በቦረኖች ሚስት የምትጠራው በባሏ ሥም ነው። የእኔ ስም ሳፎይ’ ስለሆነ በዚሁ ትጠራለች” አለኝ።ላፎይ ምን ማለት ነው?”“ቀን፤ ዘጠኝ ወይም አስር ሰዓት የተወለደ ማለት ነው:: ሳፋ ከሰዓት በኋላ ማለት ነው::”ውስጤ ለመቃወም እንዳቆበቆበ የምለው ጠፍቶኝ ዝም እንዳልኩ…“አንተ ለምን መፍትሔ ተባልክ?” ሲል ጠየቀኝ:: በትከሻዬ አላውቅም አልኩ፡፡ የሽሙጥ ፈገግታ አሳይቶ፡፡“ያለ ፍቺ ሥም ይወጣል? በኛ ቢሆን በምክንያት ሥugn ይሰጥህ ነበር። ለምሳሌ ደበሳ እንልህ ነበር:: ፀጉሩ የጎፈረ፣ ፀጉራም የሚጠራበት ነው:: ሃድ ሳፎይ ፀጉርህን ታስቆርጥህ።”“ እ- እ – አባ ገልግሌ…..?”ተቆጣኝ“አባት እንዲህ ነው ተንጠልጥሎ የሚጠራ? አብረን አደን የዋልን አይመስልም? በል ‘አቦ በል:: አቦ ነኝ ላንተ:: ሂድ ፀጉርህን ተቆረጥ ብያለሁ::”ቆይቶ ሦስተኛ ሥም ወጣለት:: የሸኖ ሰው ሁሉ “ኮርማ ብሩ” እያሉ ይጠራው ጀመር። በቋሚነት የጫት እንቱፍቱፍታ እየሰጠ እየመረቀና እየባረከ፤ በአመት አንዴ ድል ያለ ድግስ እያበላ ተቀመጠ። የተጣላ በሥሙ ይታረቅበታል፤ የተካካ በሥሙ ይካብስበታል:: ትንሿ ሸኖ ላይ ትልቅ መንግስት ሆኖ ተሰየመ::* * * *ዐይነ ሞጭሟጫው አዛውንት ያጫወትኳቸው በቅቷቸው በጠንካራ እጃቸው ይዘውኝ ተነሱ። እጃቸውን ልብ ብዬ አየሁት በደምሥር የተሞላና እጅግ የዳበረ ነው:: ከግዝፈቱ የተነሳ ህይወት የሚመላለስበት ህያው አልመስል ይላል፡፡ በስሚንቶ የታነፀ፣ ቢፈለፍሉት ጠጠር የሚተፋ ለታሪክ የቆመ እስትንፋስ አልባ እጅ:።

Related Articles

ቤባንያ ገፅ ፲፪

“ቋ!ቋ!ቋ!ቋ!…" “ምን ሆንሽ አመቴ!" አንድ ጥግ ላይ ተጎዝጉዞላት የተኛች አሮጊት ናት፡፡ “ምን ሆንሽ?” “ጥለውኝ ሄዱ" ባለፈውም የሰጠችው ምክንያት ነው:: “ጅብ ሊያስበሉኝ እዚህ...

ቤባንያ ገፅ ፲፩

በመጀመሪያ ኬኦስ ነበረ፣ የማይጨበጠውና ዉጥንቅጡ ኬኦስ የረጋቸውን ምድር(ጂኦን) ወለደ:: "እንዴት?" አይባል የሚያሰኘው የእኔ ከምንም ውስጥ መገኘት ነው፡፡ ሃይፒሪዮን ፀሐይን፣ ጨረቃንና...

ቤባንያ ገፅ ፲

ኩራዙ በየቀን ብርሃን ተውጣ ስንጥር የመሰለ ጨረር ታግለበልባለች፡፡ ዝም ብዬ ቆምኩ፡ “ሃሎ ሚስተር ባንከር" አለኝ ድምፁ ብቻ ብቅ ብሎ ዝም አልኩት፡፡ "ለከተማህ መቅሰፍት ይዘህ መጣህ?...

Comments

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *