ቤባንያ ገፅ ፫

December 15, 2023

“አምላክህ ወለድ አገድ የያዝካቸውን የድሆች ቤቶች እንዲያፀድቅልህ ነው የምትጎናበሰው? አራጣ የጭራቅ ሥራ ነው የገዛ ሥጋን ከመብላት እኩል የበላኤሰብ ልምድ::”መሳለማቸውን አቋርጠው ወደኛ አጨነቆሩ። ጉንጮቻቸው እንደወላድ ጡት የወረዱ ናቸው:: የሌባ ጣታቸውን ወደእኔ ወዘወዙ:: ሆሴዕ አልታያቸውም ማለት ነው::”አራጣ በሊታው!!” ድምፁን አቅጥኖ።”ውሻው!” አሉት እሳቸውም ድምፃቸውን በቀጭኑ እያወረዱ:: “ኣ ካካካካ…” በዚያው ድምዕ የማብሸቂያ ሳቅ ላከላቸው::“ቆይ ብቻ! ጭጋጉን በጋቢያቸው እየቀዘፉ ጠፉ ዛሬ ይቺ የእንጨት በርሜል በድንጋይ ስትወገር ማደሯ ነው” አለ።የበቃኝ መሰለኝ…* * *ጭጋጉ ተከላካይ እንደመጣበት ወራሪ ሸኖን በፍጥነት ለቅቆ አፈገፈገ፡፡ ከተማዋ ባለአንድ መስመር የበቆሎ እርሻ መስላ፣ መንገዱን ተከትላ ተቆርቁራለች:: ግንባታዎቿ በአሮጌ የጭቃ ቤቶች መንሰራፋት ላይ ተመስርተዋል:: የሽኖ መሬት ከዳተኛ በመሆኑ ቤቶቹ በቅስት ብዛት ተደጋግፈው የመስቀል ደመራን ባህርይ ይዘዋል::የመንገዱን የቀኝ ማሳበሪያ ተከትዬ ወደ ጉልት ገብታ አመራሁ:: የጉብታው ወገብ ላይ የአስታርቂኝ ማርያም ቤተክርስቲያን ተመስርታለች፡፡

“ለምን “አስታርቂኝ ተባለች?” ስል አንድ አዛውንት ጠይቂነበር።“አስታርቂኝ ያለው ጣሊያን ነው” አሉኝ:: ጮርቃነት ባደላባቸው ዓይኖቻቸው እያጨነቆሩብኝ።“እንዴት?””እንዲህ ነው:: ጠላት ጉልበት በተሰማው ጊዜ የማሪያምን ደወል ቤት ቀምቶ ዙሪያውን የባንዳ ጦር አሰፈረበት:: ‘ተንስኡ ለፀሎት’ የሚባልበትን ደወል የአስካራ ፎሌ መንፊያ አደረገው:: ህዝቡ ቂም ይዞ ሳለ ነገር መገልበጥ ጀመረ:: ጣሊያኑ በማሪያም እንደተጣላ፣ በማሪያም ለመታረቅ አስቦ ዕቃ ቤት የተቀመጠ ዕላቷን አንስቶ አዲስ ያስራው ሰቀላ ውስጥ ከተተ። አልሆነም…”“እንዴት?”እንዲህ ነው፡፡ ከወደ ስገሌ ያኮበኮበ የቁጣ ነፋስ መጥቶ የጣሊያኑን ሰቀላ ገለባብጦ የቆርቆሮ ክዳኑን ወስደ:: ነገሩ እንዳልሆነ የሆነበት ጣሊያን ቀድሞ ‘ታረቂኝ! ታረቂኝ! ታረቂኝ! አለ ይባላል:: ቀጥሎ የህዝቡ ቁጣ ገንፍሎ መግቢያ መውጪያውን ሲያጥርበት ‘አስታርቂኝ! አስታርቂኝ! አስታርቂኝ!’ አለ አሉ ጣሊያኑ:: በዚሁ አስታርቂኝ ማሪያም ተብላ ቀረች።” እሳቸውም “አስታርቂኝ ይሉ ይመስል ሞጭሟጫ አይኖቻቸውን ገጥመው ምሳጤ ውስጥ ገቡ፡፡የአፀዷን ወዝ የጠጣ የመአዘን ድንጋይ ተሳልሜ ወደውስጥ ዘለቅሁ:: የሸኖ ጭርታ እዚህ በእጥፉ ተከናውኗል:: እድሜ የጠገቡ የዕድና የወይራ ዛፎች ከዳተኛው መሬት ላይ ተንስራፍተው ቆመዋል:: ያልቻሉት ባህር ዛፎች ተፈንችረው ሥራቸው የዛር ራስ መስሉ ተንጨፍሯል፡፡አብዛኛው ትዝታዬ ከዚች ግቢ የማይወጣና ከእምነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ፈተና ሲያስጨንቀኝ የተሳልኩበት የማሪያም ማመላከቻ የማደሻ ቀለም ተከናንቦ የቤተክርስቲያኑ ግድግዳ´ ላይተኝቷል። ሲከፋኝ የሚያፅናናኝ የዚህ ግቢ አፀድ ነው:: አንድ የወደቀ ግንድ ለስንት እና ስንት ነፍሳት እንዲሁም ጥቃቅን ተክላት መጠቂያ እንደሚሆን የተረዳሁት ደጋግሜ እየመጣሁ አትኩሬ በመመልከት ነው:: ቀያይ ጉንዳኖች ኃላፊነትን በመወጣት ትጋት ግዳይ የጣሉትን ነፍሳት ሆነ የቅጠል ቅርድድ ወደ አንድ የግንድ ሽንቁር ለማስገባት ሲጥሩ ስመለከት የእስከዛራው የህይወት ምልከታዬ አንሶና ጠብቦ ይታየኛል:: የህይወት ተአምር ያለው እጅግ ቀርበው የሚመለከቷቸው ጥቃቅን ነዋሪዎች ዘንድ ነው:: ይሄ የህይወት ኃላፊነትና ትጋት እንዲከናወን የትኛው አካላቸው ላይ በተፈጥሮ ህግነት ሰፈረ ይሆንን ቅጠል በሚረግፉበት የጥጋብ ዘመን ላይ ሆነው እንደምን ደረቁንና ንፉጉን ወቅት ተነበዩ? አስተማሪ አንጋፋዎች፣ ተማሪ ውጫጮች ይኖሯቸው ይሆን? እናት አባት፣ አይት ምራት፣ እንጀራ አባት እንጀራ እናት… ይኖራቸው ይሆን?ምን እያየህ ነው፤ ጃል?” አለ እንድ ድምፅ:: ከተመሰጥኩበት ተናጥቤ አየኋቸው:: አይነ ሞጭሟጫው አዛውንት ነበሩ። ነገርኳቸው:: በጠንካራ እጃቸው እጄን ይዘው ወደ መጠለያው እያቀኑዝሃቲ ጥበብ ፈጠረተነ ይላሉ አባቶች:: ይሄን ሁሉ መርምረው መድረሻው ቢርቅባቸው ነው ‘አንዲት ጥበብ ፈጠረችን’ ያሉት::”ስለብዙ ነገር አጫወቱኝ…”…የተፈጥሮን ረቂቅነት የሰው ልጅ ሰፍሮ አይጨርሰውም። የፊት የፊቱ ላይ ስም እያወጣና ግልብ ምርመራ እያካሄደ በተቃራኒው ይጠፋ እንደሁ እንጂ ተፈላጊው ቦታ ላይ የሚያደርስ አቅም የለውም።እስኪ ልብ ብለህ አጢነው፤ እዚህ ቤተ-እግዚአብሔር ስንመጣ የምናገኘው ሠላም መተኪያው ምንድነው? ብድራችን እንደተከፈለ፣ ዕዳችን እንደተሰረዘ፣ ችግራችን እንደተቀረፈ ሁሉ ፍፁማዊ ሠላምና መፅናናት የምናገኘው እንዴት ነው? አንድ ሙጭቅላ ከእናቱ እቅፍ ሌላ ርስት አለው? የሰው ልጅም እንደዚያው ነው፤ በእምነት አምላኩ እቅፍ ውስጥ ከማረፍ ውጭ የአለም ውጣ ውረድ የሚያሻጡን ሰላም አይሰጠውም.. ወዛም የአይኖቻቸውን ዳርቻዎች መሃረብ አውጥተው ጠራረጉ። በምፀት ፈገግ ብለው ጨዋታቸውን ቀጠሉ“ሳጥናኤል ቢቸግረው “አነ ፈጣሪክሙ” (ፈጣሪያችሁ እኔ ነኝ) አለ። የሚሰማው የሚለማው ቃሉ ደርሶ ቢያምነው እንኳ! ቅድም አንተ ያየኸውን የጉንዳን ማህበር ምን ሊያደርገው ነው? የፍጥረተ አለሙ ስፋት እራሱን ኢምንት አድርጎ ያጠፋዋል። የእግዚአብሔር ጥበብ መለኪያው በሚሰማውና በሚለማው ተለክቶ አይታቀብም:: ውጫጩና ቁጫጩ ሁሉ በፈጣሪው ዘንድ ተቆጣሪና የምስጋና አስራት አቅራቢ ነው::”ሲያወሩት አላውቀውም፤ ግን ይገባኛል:: የማላውቀው ነገር እንዴት ገባኝ፣ እንጃ! የተንጨፈረሩ የቅንድቦቻቸውን ፀጉሮች እያየሁ ዝም!”የማነህ ልጅ?” ጠየቁኝየምመልሰው ግራ ገብቶኝ ለከት አልባ እጃቸውን እያየሁ ዝም አልኩ።“አባትህ ማነው?’“አባት የለኝም”ያዘኑ መሰሉ።“እናትህሳ?””እናት የለኝም?’“የት ሄዱ?”

እኔ.. ከመጀመሪያውም ያለኝ የእንጀራ አባትና የእንጆ እናት ነው::” ለማስረዳት የከበደ ሆነ“እንዴት? እንዴት?” አይናቸውን ያበሱበትን መሃረብ የኮ ኪሳቸው ውስጥ ከተቱ፡፡“የመጀመሪያ እንጀራ አባቴን አላውቀውም እሱ ድንገት ተነስቶ ወደ ትውልድ አካባቢው ሲሄድ ለጥቂት ጊዜ ሚስቱ ጋሽ ይማምን አገባች። ጋሽ ይማም ደግ ሰው ነው:: ቁጭ ብሉ እየተወዘወዘ ሲዘይር ማዳመጥ ደስ ይለኝ ነበር። “ልጁ” ይለኛል:: ከቤት ወጥቶ ሲገባ ቢያጣ ቢያጣ ከረሜላ ይዞልኝ ይመጣል::“ልጁ፣ ና ከረሜላ ምጠጥ” ይለኛል፡፡ለሱ ጫቱን ይዞ ይቀመጣል፤ ይዘይራል፡፡ የድምፁ ነገር ሌላ ነው:: የተነጠፈለት ላይ እንቅልፍ እስኪወስደኝ አደምጣለሁ። አንዳንድ ጊዜ ብቻ ጫት የሚቋደሱት ጥቂት ስዎች ይመጣሉ። አምላኩን በአንቱታ ይጠራል።“እየመሩ አመጧችሁ? ይሁን!” ይላል፡፡አንድ ቀን ሚስቱ ልሂድ አለች፡፡ ጣት ለጣት ተጣምረው በፍቅር እያወጉ አድረው በጠዋት አሳፍሯት ተመለሰ፡፡“እርሳቸው ካሉ ምን ይሆናል?” አለ፡፡“አሜን፤ አሜን!ሁሉም ይሄደዋል ያን ረዥም ጉዞ፣የሌለው ባዶውን ያለው ስንቁን ይዞ፤አ-ሜ-ን! አሜን!!እንደው ልንገር እንጂ ታዲያ ለማን ልንገርሁሉም ስደተኛ አንቱ ነሁ ባላገርአ-ሜን —–አ-ሜን!!”

Related Articles

ቤባንያ ገፅ ፲፪

“ቋ!ቋ!ቋ!ቋ!…" “ምን ሆንሽ አመቴ!" አንድ ጥግ ላይ ተጎዝጉዞላት የተኛች አሮጊት ናት፡፡ “ምን ሆንሽ?” “ጥለውኝ ሄዱ" ባለፈውም የሰጠችው ምክንያት ነው:: “ጅብ ሊያስበሉኝ እዚህ...

ቤባንያ ገፅ ፲፪

“ቋ!ቋ!ቋ!ቋ!..." “ምን ሆንሽ አመቴ!" አንድ ጥግ ላይ ተጎዝጉዞላት የተኛች አሮጊት ናት፡፡ “ምን ሆንሽ?”“ጥለውኝ ሄዱ" ባለፈውም የሰጠችው ምክንያት ነው:: “ጅብ ሊያስበሉኝ እዚህ...

ቤባንያ ገፅ ፲፩

በመጀመሪያ ኬኦስ ነበረ፣ የማይጨበጠውና ዉጥንቅጡ ኬኦስ የረጋቸውን ምድር(ጂኦን) ወለደ:: "እንዴት?" አይባል የሚያሰኘው የእኔ ከምንም ውስጥ መገኘት ነው፡፡ ሃይፒሪዮን ፀሐይን፣ ጨረቃንና...

Comments

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *