ቤባንያ ገፅ ፩

December 13, 2023

ቤባንያ

ገፅ አንድ

hማና ሸኖ

…በሸኖ ጭጋግ መካከል ሰንጥቆ የሚያልፈው ቀስተደ ደመና፤ ሀብል መስሎ ብዙ የጤዛ እንክብሎችን ይሰካካል። የሸኖ ሰማይ ገና መሬትን “ያላወቀ” አፍላ ነው፡፡ መሬት ከጎን አጥንቱ አልተፈለቀቀችም። ሰማይ ጭጋጉን እየባዘተ አጮልቆ ኮረዳይቱን ምድር የሚያያት ይመስላል፡፡ ከሰማይና ከምድር ሩካቤ የሚወለዱት የግሪክ አማልክት የህላዌ ደጃፍ ላይ ወረፋቸውን ሰድረው ቆመዋል፡፡ (Titans…) – (Cronus) (Saturn) (Zeus) (Jupiter) & (Ocean) (Tethys): (Hyperion) : (የፀሃይ:የጨረቃና የፀሀይ ግባት አባት አባት፡፡) ጢሚስ (Themis)፣ የአትላስ (Atlas)፣ የፕሮሚተስ (Prometheus) አባት… ሁሉም አንጋፋ አማልክት የተከሰቱ ማይመስልበት ድንግል ተፈጥሮ።
ኳ ኳ ኳ ኳ
ወደ አሁን…

…ሊስትሮው ሳጥኑ እስክትንጫጫ በጫማ መጥረጊያ ብሩሽ ቀጠቀጣት፡፡ እግሬን አቀያይሬለት ወደ ሀሳብ ማስከንተሪያዬ ል’ነገ ስል እስሬ የተጨበጠው ጫማ ጠራጊ እንደመነጫነጭ እያለ……ክረምቱ ከወዲሁ ጀምሮ እንዴት ይዘለቃል? ምን ይበላል? የት ይታደራል? እርስዎ ብቻ መጣሁ፣ መጣሁ የሚለው ዝናብ ሳይበግርዎ ጫማ ያስጠረጉኝ።”የሚያኮራምት በሽታ የተጠናወተው እንጂ ለሥራ የተጨበጠ አይመስልም:: እንደ አዲስ አካባቢዬን አየሁት:: ጭጋጉ ከመሬት እየተጥመለመለ ይፈላል:: ምድር ለምድር ይንፏቀቃል። የተንጋለለ አህያ መስሎ እግሩን ወደላይ እንዳንጨፈረረ ሁሉ ጀርባውን ኮረት ላይ ይፎክታል፡፡ ቀሰስተኛ አመድ የሚቦን ይመስላል። በዚህ አየር ሁኔታ ማንም ሰው ጫማ አያስጠርግም። ጫማዬ ሲደበዝዝ ደስ የማይለኝ እኔ ብቻ ነኝ? የቆሸሸ ጫማ፣ ምን ልብስ ንፁህ ቢሆን ያደፈ ማስመሰሉ እርግጥ ነው፡፡ ከዚያም አልፎ ያልተጠረገ ጫማ ፊት ያጎሳቁላል፤ ተስፋ ቢስ ያስመስላል።ኳ!ኳ!ኳ!ኳ!ጫማዬን ሳይሆን ቀኔን ያበራልኝ መሰለኝ።“የሚበላውና የሚያድርበት የሚያሳስበው ሆሴዕ ብቻ ነው። አለ ቋጠሮ መስሎ እስሬ ሥር የተቀመጠው ጫማ ጠራጊ።“ሆሴዕ! ሆሴዕ!” ጫማ ሲቦርሽ ደረቱን በፍጥነት የሚያ ይመስላል፡፡“ለመሆኑ ሆዕሴ አለ?’ ስል ጠየኩት።“ያው ንጉስ ጊቢ ላይ የእንጨት በርሜል ውስጥ ያድራል፡፡ ተቻለስ እንደሱ ያለሃሳብ፣ ያለፈ ያገደመውን እየተሳደቡ መኖር ይሻል ነበር።””እንደ ዲዮጋን? እንደ ፈላስፋው?””እ?” ደረቱን ማከክ ገታ አደረገ።”አይ ወዲህ ነው”ለሸኖ የምመኝላትን ያሸበረቀ ጥንታዊነት ሆሴዕ ያሟላ መስሎ ተሰማኝ። እንደውሻው ዲዮጋን አላፊ አግዳሚውን ሳይመርጥ የማንቂያ ስድብ ሊያዘንብ? ለህብት ንብረት ግድ ሳይኖረው በእንጨት በርሜል ውስጥ ሊኖር?    ኳ !ኳ!ኳ!ኳሊስትሮው ብብቻውን ለመጨረሻ ጊዜ አከከ የማውቆት መሰለኝ””ይሆናል?” ከአዲስ አበባ ከመጣሁ ሰዓት ጀምሮ ሽኖን እንዳላደኩባት፣ እንዳልኖርኩባት ሁሉ የሚያስታውሰኝ ማጣቴ ሳይቆጨኝ አልቀረም። ደስ አለኝ።”የት?” እንደተኮማተረ አንገቱን አፍታቶ አስገገብኝ፡ አይኖቹ ይፈትሹኛል።”የት ይመስልሃል?””እኔማ ከሽኖ በተቀረ ሌላ አገር አላውቅም:: አዲስ አበባን እንኳን ድሮ ወደ አገር ቤት ስሄድ ሎንቺና ልሳፈርባት ነው የማውቃት”

ሽኖ አይንና ጆሮዎች አንዱ ይሄ ሊስትሮ ሳይሆን አይቀር “”እዚሁ ሽኖ?” እንደተጨበጠ ተቁነጠነጠ“አዎ ሁለመናው ጭጋግ ባደበዘዘው መካከል የጫማዬን ማብረቅረቅ እያደነቅሁ፡፡ የተቦረሸ ጫማ የተፈጥሮ ብርሃንን ተቀበሉ ከማንፀባረቅ ውጭ የራሱን ጨረር ከውስጡ ያፈልቃል? ካልሆነ ታዲያ…..የት? ማንጋ? የማን ልጅ ነዎት?”የማን ልጅ እንደሆንኩ እንኳ እኔም አላውቀው? ልለው ፈልጌ ተውኩት:: የእንጀራ እናቶቼንና የእንጀራ አባቶቼን ልዘርዝርለት ይሆን? ስሜቴ ጠየቀ።”የት አሉኝ?””ኮርማ ብሩ ግቢ” አልኩ ሳላስበው፡፡”ባለውቃቢው?’ ተነሳ”እዎ “ተነሳሁ፣ ኪሴን ፈተሽኩ’ያ ልጅ ነዎት እንዴ?”ምን ይጎረጉራል? ተናደድኩበት? አስር ብር አዉጥቼ ሰጠሁት።”ከዚህ ከወጣሁ ቆየሁ፤ ሰው ብጠይቅህ ታውቃለህ?””ይመስለኛል” አሁንም እኔ ላይ በአይኑ እንደተጣበቀ የተጣ እግሩን አላቅቆ ተነሳ።“ምስጢር የምትባል ልጅ…” አሁንም ልጅ ናት? ለምን ልጅ አልኳት? የሽኖ አቧራ የቃመ እግሯ… ከቁርጭምጭሚቷ በላይ ፓስቲውንም የክልክሉንም ተረፈ ዘይት ተቀብቶ ይወዛና ነጠላ ጫማዋን ሽፍን ሲያስመስለው ሁሉ ትዝ አለኝ፡፡“አውቃታለሁ”የሊስትሮ ሥራው የቀዘቀዘው በአየር ሁኔታ ሳይሆን ለወሬ ትኩረት በመስጠቱ ሆኖ ተሰማኝ።“ድሪባ አስረግዟት፣ አላውቅልሽም ብሏት፣ ሰው አይንሽን ላፈር ብሏት…..”የኔዓለምስ?…””የኔዓለም?” ብሮች እያወጣ…”የምስጢር ጓደኛዋ ናት”“እ-እሷኮ የሆሴዕ ነበረች የሚሏት?…”የሰጠኝን መልስ ተቀብዬ ሳልቆጥር ወደኪሴ። የሰው ገመና መስማቴ መንፈሴን አስቆጣው:: መጠየቅ የፈለኩት የምስጢርንና የኔአበባን ሁኔታ አልነበረም። ቤባንያስ? ማንን ወድዳ? ማንን አምና? በማን ተጠልታ? በማን ተካደች?… መቼም የቤባንያ ታሪክ ተራ መውደቅ፣ የወጣትነት ገድል አይሆንም። ሁሌም በህልሜ እንደማየው ከእሷ ጋር መባረር ቀስ በቀስ መሬትን በእግር ከመተምተም አልፎ በመጫሚያ መሸረፍ… በኋላም አየር ላይ መንሳፈፍ የሚከተልበት ተአምር መሆን አለበት፡፡ቤባንያ፣ ቤባንያ፣ ቤባንያ…

Related Articles

ቤባንያ ገፅ ፲፪

“ቋ!ቋ!ቋ!ቋ!…" “ምን ሆንሽ አመቴ!" አንድ ጥግ ላይ ተጎዝጉዞላት የተኛች አሮጊት ናት፡፡ “ምን ሆንሽ?” “ጥለውኝ ሄዱ" ባለፈውም የሰጠችው ምክንያት ነው:: “ጅብ ሊያስበሉኝ እዚህ...

ቤባንያ ገፅ ፲፪

“ቋ!ቋ!ቋ!ቋ!..." “ምን ሆንሽ አመቴ!" አንድ ጥግ ላይ ተጎዝጉዞላት የተኛች አሮጊት ናት፡፡ “ምን ሆንሽ?”“ጥለውኝ ሄዱ" ባለፈውም የሰጠችው ምክንያት ነው:: “ጅብ ሊያስበሉኝ እዚህ...

ቤባንያ ገፅ ፲፩

በመጀመሪያ ኬኦስ ነበረ፣ የማይጨበጠውና ዉጥንቅጡ ኬኦስ የረጋቸውን ምድር(ጂኦን) ወለደ:: "እንዴት?" አይባል የሚያሰኘው የእኔ ከምንም ውስጥ መገኘት ነው፡፡ ሃይፒሪዮን ፀሐይን፣ ጨረቃንና...

Comments

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *