ቤባንያ ገፅ ፯

December 22, 2023

ክፍል 4

ለማና ወዳጄ ልቤ

ቤባንያ የክልስ መልክ አላት፡፡ ገና ዘጠነኛን እንዳለፍን እኛ ክፍል ቁጭ ብላ አገኘኋት። ልቤ “ባትጋሩኝ አለ ተሽቀዳድሞ:: እንደአልማዝ’ እንደዕንቁ፣ እንደ እንቆጳዚዮን… ከውስጧ የሚወጣ አንፀባራቂ ብርሃን አላት፡፡ የተሰባበረ ጨረር ውስጧ እየተስለከለከ አንዳች ትርኢት ያሳያል፡፡ቡኒ ፀጉሯ፣ ጭንቅላቷን መታ እያደረገች ስትቆጣው መስመር የሚይዝ ልምጥምጥ _ ፀጉር ! ሁሉ የሚያየው ውበት ተጠምቃለችና የማይወዳት ወንድ ተማሪ የለም፡፡ ብቻ ሴቶቹ………….ደቻሳ ደፍሮ ቀረበ። ፀጥ ባለ ፊት እያየች አልተቃወመችውም:: የተቀረነው እንደጥፋት አየንባት ‘ያለ አንድ ሳንካ አይፈጠር አልንባት፡፡ ደቻሳ ሽር ጉድ ይልላታል፣ እርሳስ ሲወድቅ ቀድሟት ያነሳል፣ ወደ ቤት ስንሄድ ቦርሳሽን ካልያዝኩ ይላል፣ እሷ ትምህርቷን ስትከታተል፣ እሱ እሷን ይከታተላል፡፡ ጉልበታም ቢጤ ስለሆነ እኛን ያስፈራራል፡፡አንድ ሰሞን ለተከታታይ ቀናት ከትምህርት ቤት ቀረ። ትምህርቱንስ ትቶታል በቤባንያ የሚያስጨክን ምን አደጋ አጋጠመው? ስንል ቆየን። ደቻሳ ወደ ትምህርት ቤት ቢመለስም ቤባንያ ስር ሽር-ጉድ ማለቱን ተወው:: ፊቱ ላይ እንዳንድ የተስለ ፈለጎች በማየታችን ሁኔታው ግራ አጋባን፡፡ በኋላ ወሬው ሲጣ የቤባንያ ወንድሞች ከቤባንያ ጋር አግኝተውት ደብድበውት ነው አሉ::አደጋ!!እኔ ብቻ አደጋውን ለመጋፈጥ ቆረጥኩ፡፡ ቤባንያን ሳይት የምሞትላት አላማዬ ሆና ቁጭ ትላለች። እናት፤ ኃይማኖት፣ ርስት ሚስት… እንደ ቤባንያ አቅል ያስታሉ? ደም ዝውውር ያሰናክላሉ? ጉልበት ያፈሳሉ?… ታዲያ?አማረኝ:: ብናኝ ፀጉር ነጫጭባ ሁሉ ጡንቻውን አስቆጥቶ፤ ደሞወንድሞቿን አየኋቸው:: ጣሊያን ሽኖን ወረረ! ብዬ መለፈፍ እንደማይለዩ ሁሉ ተበታትነው ቤባንያ ከማን ጋር እንደምትወጣ፤ እንደምትገባ ያያሉ፡፡ ማሪያምን “ታረቂኝ ያለው ጣሊያን ፤ በኋላም “አስታርቂኝ” ብሎ ያልተሳካለት ሶልዳቶ ለበቀል ሥራ ዘር ማንዘሩን ያሰማራ መሰለኝ፡፡ እንግዲህ ዕጣፈንታዬ እንደአያቶቼ በሶልዳቶ ዕጅ ነፍሴ እንድታልፍ ተቆርጦ ይሆን እንደሆን አያለሁ እንጂ ቤባንያን አልተውም።“ተዉ፤ ወንድሞቼ ይገድሉሃል” አለች በተንተከተከ ስሜት፡፡ በፈዘዘ ፊት፣“ይግደሉኝ!”የማይደፈረውን የትምህርት ቤት አጥር ከቤባንያ ጋር ሆኜ ጣስኩት፡፡ እንደ አዳኝ ተኩላ ከየአቅጣጫው ቀይ ጉንዳን መስመር ሰርቶ ሲመጣ ይታየኛል፡፡“ኦ! አምላኬ ነፍሴን ተቀበል፤ ቅድስት ሆይ በጣሊያን አስካሪ ላይ ያስነሳሽው የሰገሌ ቁጡ ነፋስ ዛሬ ያስፈልጋል!!”“አላልኩህም?” አለች ቤባንያ

አንድ ሁለት ቡጢ እንዳረፈብኝ፤ ገና የቡጢውን መምጪያ አቅጣጫውን ሳልለየው “ተዉ! ተዉ! ተዉ!” የሚል ድምዕ ተሰማ፡፡“ምንድነው?”“እሱ ጅል ነው! ምንም አስቦ አይደለም’እሷ ፊት ጅል ከሚሉኝ ቢገድሉኝ የተሻለ ነበር፡፡ መስዋዕትነቴ ዋጋ አግኝቶ እንደ ደቻሳ ሳምንት የሚያስተኛ ጉሽምታ በወረደብኝ፤ ኧረ በገደሉኝ ጥሩ ነበር።የሸኖ ቀይ ጦር ጉዳት ሳያደርስብኝ! እንደውም ሁሌም ከእሷ ጋር መሆን እንዳለብኝ፣ ግን የሚከታተላትን ተከታትዬ ለእነሱ ወሬ ማቀበል እንዳለብኝ ተነገረኝ፡፡ አቧራዬን አራገፉልኝ::ወድቄ ነበር _ እንዴ? ስወድቅ _ ቤባንያ አይታኝ ይሆን? ለጀግንነት ያልኩት በጅል ግብታዊነት ተመዘገበ። የሚስቅ እንጂ የሚያደንቅ ጠፋ!”ቤባ”“አትጥራኝ!”ምን አደረኩ? ልሞት ሄጄ ስላልሞትኩ? ከመሞት በላይ ለመሞት መቁረጥ ውስጥ ጀግንነት የለም? ከጀግንነት መስዋዕት ወደ ጅል ድል ማን ከተተኝ? ቤባንያ እኔን ማስቀደም ሆነ ማስከተል ኩራት አልሆንላት አላት፡፡”ቤባ”“አትጥራኝ”“አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ስንወጣ ሆነ ብዬ አቀፍኳት:: ተመናጨቀች። በሥልት የሚያጠቁት ወንድሞቿ ሲመጡ፡፡”“እኔ ጅል አይደለሁም” አልኳቸው፡፡ለተወሰነ ጊዜ መላዋ ሽኖ ፀጥ አለች:: አምላኮቿ ሁሉ የሚከተለውን እርምጃ በመጠበቅ ፈዘው ቀሩ:: ጆሮዬ ውስጥ ትልቅ ጩኸት ተተከለ። ቤባንያ እንኳን የመነቃነቂያ ጅስም ያላት ሳትመስል ለዘልአለሙ ቆማ ቀረች።ጅል የሚታወቀው ጅል አይደለሁም ሲል ነው” አለ አንድ ወንድሟ። ሁሉም ‘አሁን ሳቁ’ የተባሉ ይመስል እኩል አምባረቁ!ቤባንያን አየኋት፣ ያዘነችም የተናደደችም ትመስላለች፡፡ ወይ ትዘን፣ ወይ ትናደድ እንዴት ሁለቱንም?ወደ ትምህርት ቤቱ ተመልሼ በጓሮ በር ወጣሁ። እዚያ የማሪያም ቤተክርስቲያን አለች:: “አስታርቂኝ” ዛሬ የሶልዳቶ ሳይሆን የኔ ተማፅኖ ሆኗል፡፡ቦርሳዬን _ ለሸክም _ አመቻችቼ ደጇን ተሳለምኩ፡፡ ውስጤ የሚያነበንብ ማንነት አለ፡፡በከመ ይቤ በመጽሐፈ ፍልሰታ፣በእግዝእትነ፣ ቅድስት ድንግል በ፪ኤ፣ማርያም ወላዲተ አምላክ።(አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ፣በድንጋሌ ነፍስ የፀናችየክብርት እመቤታችንን የፍልስቷን ነገር በሚናገር መጽሐፍ እንደተናገረ።)ወደ አፀዷ ዘለቅሁ፡፡በሸኖ ከዳተኛ መሬት የተነሳ ተሸንፈው የተፈነደሱትን ዛፎች ብቻ ቆጠርኩ:: አስራ አምስት ደረሱ። ሁሉም ከቤተክርስቲያኗ ህንፃ በተቃራኒ የወደቁ ናቸው:: የማሪያምን ተአምር የሚያሳይ ስብከት አድርግ ቢሉኝ ከእነዚህ ዛፎች አወዳደቅ ተነስቼ የሚዳሰስ ትምህርት እሰጥ ነበር ።

“ቅድስት ሆይ፤ ከዚህ እንደጅል አመቆጠር አዙሪት አውጪኝ”እዚች ግቢ ውስጥ ብዙ ችግሮቼ እንዲቀረፉ ፀልያለሁ:: የተደናገጠ እዚህ እስኪያገኝ ድረስ አፀዷን ሙጥኝ ብያለሁ፡፡ አንዳንዴ መፍትሔው መቁረብ ሆኖ አገኘዋለሁ፡፡ አቆርባለሁ:: ስቆርብ ሰላም አገኛለሁ፡፡”ቆይ ብቻ! ይቺ ቁርባን ያዘችኝ እንጂ ልክ ማስገባቱንማ አውቅበት አልነበር?” ትላለች የእንጀራ እናት፡፡ (ክፉዎቹ እንደራ እናቶች አትጠይቁኝ፡፡ ውስጤም ማመላከቻ የላቸውም።)አልፎ አልፎ አቀበታም መንገድ እንደመጓዝ፣ የተራራው ወገብ ላይ ትንሽ ደልዳላ መሬት እንደማግኘት ቁርባን የእረፍት ጊዜ ይሰጠኛል። ማንም ` አይመታኝም፤ የሰው ትራፊ አልበላም፣ የሚቆረጥመው የሽኖ ቀዝቃዛ ውኃ ውስጥ አልዘፈዘፍም፤ ከአልጋ አልወርድም፣አንድ ቀን አይናቸው የሚከስምባቸውን አዛውንት ጠየኳቸው:: ለሁልጊዜውም የሚሆን ቁርባን የለም? ለሁልጊዜውም መቁረብ አይቻልም?”በድን የመሰለ ግዙፍ እጃቸውን አወናጭፈው ዝንብ አባረሩና “ምነው ልጄ? ሃሳብህ ጥሩ ነው፤ ግናስ ገና ሙጭቅላ ነህ ምን አሳሰበህ?””እናቴ እንዳትመታኝ፣ ትምህርት ቤት እንዳልሄድ፣ ትራፊ እንዳልበላ፣ ከአልጋ እንዳልወርድ።”

እንደምፈልግ እንኳን ጠፍቶኝ ወደ ቤቱ ለመሄድ ተነሣሁ፡ ቅልል ብሎኛል፡፡ የዋናውን በር አቅጣጫ ይዤ በሀሙስ ገበያ በኩል ቀስ እያልኩ ወደ ቤቱ ለመሄድ እንደጀመርኩ አንዲት ነጠላ የተከናነበች ሴት አይኔን ሳበች:: ከሴቶች በር አቅጣጫ ወደ እኔ ትመጣለች:: አስክነሳ እየጠበቀች ይመስላል፡፡ አተኩሬ ስመለከታት ቀና አለች፡፡ቤባንያ!ህመም እስኪሰማኝ ልቤ ደነገጠች:: ቆምኩ”ሂድ! ሂድ!” አለችኝ:: የማደርገው ጠፍቶኝ እያየኋት ወደ ኋላ ስሄድ የወደቀ ግንድ ጠልፎ በጀርባዬ ጣለኝ:: ቀልጠፍ ብዬ ተነሳሁ! የማደርገው ጠፋኝ፡፡ እራሴን የመፈመርኩበት ጥበብ የት ገባ? ምን ዋጠው? ቤባንያ በውስጤ ያላትን ቦታ የሚክድ መዳረሻዬን ምን በላው።“ሂድ! ሂድ!” እያለች ትከተለኛለች:: አፀዱን እንዳለፍኩ ጎን-ጎኔ መራመድ ጀመረች። የሚያማምሩ የእግር ጣቶቿ ከጥልፍልፍ ጫማዋ ማበቻ ብቅ-ብቅ ብለው ሲታዩ ሌላ የልብ ህመም ይሆናሉ፡፡ የሚረግጡት እየመረጡ አንዴ ወደ ግራ አንዴ ወደ ቀኝ ይመራራሉ::ከቤባንያ ጋር ብዙ የህልም ጉዞዎችን አድርጌአለሁ:: እንደ እውኑ አስቀያሚ አይደሉም። በህልም ወደየትም ቢዞሩ የቤባንያ ፊት አለ። ፈንጠዝያው ለከት የለውም:: ሰዎች ሁሉ በህልም ውስጥ ወደ ጥላነት ይለወጣሉ፡፡ ዓለም ማድመቂያዎች ናቸው::የእውን ጉዞ እንደዚያ አይደለም:: እጇን እጄ ቢነካው ሰብሰብ ታደርገዋለች:: ለማቀፍ እጄን ትከሻዋ ላይ ጣል ባደርግ “አውርድ አንተ ጅል” ትለኛለች። “ለመሞት ቸኮልክ”በህልም መውድቅ የለም፣ ማፈር አይከተልም፡፡የደብተር ቦርሳዬን ከግራ ወደቀኝ አዙሬ እጄን ትከሻዋ ላይ ጣል አደረኩ::

Related Articles

ቤባንያ ገፅ ፱

"እኔና አንቺ?"ጅል' ሳቅ ፈለቀች፣ አሳዘንኳት፤ አፌ ላይ ሳመችኝ። ምንድነው ተአምሩ? ከንፈሬና ልቤን የሚያገናኝ ምን መስመር ተዘርግቷል? መቼ ይሆን ዳግም የምትስመኝ?“ኧረ ሸኖዎች። ብዙ...

ቤባንያ ገፅ ፰

“አውርድ አንተ ጅል ትላለች ብዬ ጠበኩ ዝም አለች የእነሱን ሠፈር ርቀን ሄደናል፡፡ የጉልት ገበያ በአመሻሽ ግብይት እንደመሞቅ ብላለች፡፡ የዕለት ፍጆታዎችን ለመሸጥ ቁጢጥ ቁጢጥ ያሉ ሴቶች...

ቤባንያ ገፅ ፮

“ታዲያ ምን ሆኖ ነው? እቃጠለኝኮ ተቃጠልኩ ውሃ የለም?” እኔ እቀጥላለሁ፡፡ "ከገንዘብ ይልቅ የዕታ ለዕቃ ልውውጥ እንደሽኖ ላሉ ነባር ከተሞች ውጤታማነቱ ተረጋግጧል፡፡ (ማነው...

Comments

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *