ቤባንያ ገፅ ፮

December 20, 2023

“ታዲያ ምን ሆኖ ነው? እቃጠለኝኮ ተቃጠልኩ ውሃ የለም?” እኔ እቀጥላለሁ፡፡

“ከገንዘብ ይልቅ የዕታ ለዕቃ ልውውጥ እንደሽኖ ላሉ ነባር ከተሞች ውጤታማነቱ ተረጋግጧል፡፡ (ማነው ያረጋገጠው፣ ቢሉኝስ? እንጃ!) ወይም በጨርቃ ጨርቅ፣ በዛጎል በጥይት፣ በአሞሌ ጨው በቁርጥራጭ ብረቶች ፍፁማዊ ተፅዕኖ ነፃ ያደርጋል::” መገበያየት ከመንግሥትና
ከጃቤዎች ፍፁማዊ ተፅዕኖ ነፃ ያደርጋል።”

እንግዳው የባንክ ሰው አግዳሚ ላይ ተጋድሞ የሳንሳ ተይዞ ሲወጣ በደከመ ድምፅ…

ይሄን ቅርንጫፍ መጋዘን አድርጉት፣ ጨርቅ፣ ኣሞላ ጨው’ ዛጎል፤ ጥይት፤ ቁርጥራጭ ብረት… አከማቹበት ከእንግዲህ የሚያዋጣው ይሄው ነው::” ይላል:: የታባቱ!!

ሊስትሮው ለአፍንጫ የተቋጠረ ጥቁር አዝሙድ መስሉ ሳጥኑ ስር ተጥሏል። ስደርስ ተንደፋደፈ:: ከተቋጠረበት ሆኖ በጨርት መቀመጫውን መታ መታ አደረገ፡ ማዕዳቱ`ኮ ነው፡፡ ቁጭ አልኩ፡፡

የሰው ልጅ አቅምና የማጥፋት ኃይሉ የተመጠነ መሆኑ በጀ እንጂ በትንሽ መከፋት ስንቱን ሲገለባብጥና ከሰልፍ ውጭ ሲያተረማምስ በኖረ ነበር:: የስሜት አፀፋችን ለከት አልባ መሆኑ ‘ተደፈርን፣ ተዋረድን’ ባልን ቁጥር የአርማጌዶን ጦርነት እያስነሳንም የማንረካበት እራስ ወዳድነት ውስጣችን አለ፡፡ ምንድነን?

እግሬን አንዱን አውርጄ ሌላውን ሰቀልኩ:: ከሊስትሮው ጋር ማውራት አልፈለኩም።

“ትናንት እርስዎ ጫማዎን አስጠርገው ከሄዱ በኋላ…” የወሬ ጉጉት መፍጠሪያ አንጓ ላይ ንግግሩን ገታ::

ሳልፈልግ “እ?” አልኩት፡፡ ይሄ ቋጠሮ“ብዙ ሰዎች እየመጡ ጫማ አስጠረጉኝ:: ስለአንቱ ወሬ ለመለቃቀም እኮ ነው”“ስለኔ ምን?”“አንዳንዶቹ የገንዘብ ሱቅ ከፍቷል አሉ ይላሉ::”ወይ ጉድ! ለነገሩ ባንክ የገንዘብ ሱቅ ነው:: እንደውም ትክክለኛ ስያሜ ይመስላል።“እ-ሺ?” አልኩ ሳልወድ በግድ፡፡“አንዳንዶቹ የአራጣ ሱቅ ነው ይላሉ::” አባ ዲሪባ አራጣ በሊታ ትዝ አሉኝ።ወይ መከራ! ለነገሩ ትክክል እኮ ናቸው:: ዘመናዊ የአራጣ በሊታ መሥሪያ ቤት ነው፡፡ ገንዘብ ለሚያስቀምጡ በጥቂቱ አራጣ ያነካካና፤ ለሚበደሩ አራጣ ይጭናል። ይሄው ነው፡፡“እኔ በመሃከል ሸቀልኩ::”ይሄው ነው:: ወሬ አገናኝ ሁሌም ሸቃይ ነው፡፡። ኳ! ኳ! ኳ!እግሬን አለዋወጥኩ፡፡“አንዳንድ ሰዎች ስልክ ቁጥራቸውን አስቀምጠዋል።”“ለምን?” ግዴለሽ ለመሆን እየፈለኩ አልቻልኩም፡፡ ይሄ ኮምታራ ጫማ ጠራጊ በወሬ አቀራረብ በልጦኛል።“አንዳንዶቹ የቤት ሠራተኛ ከፈለገ እያሉ ነው:: አንዳንዶቹ ለቢሮ የፅዳት ሥራ ለመቀጠር ነው አንዳንዶቹ ግን…” ቁራጭ ሳቅ ወረወረ“እ? ምን አሉ?””ሚስት ከፈለገ ብለዋል፡፡…አይ ሽኖ! አይወርጅና ስኮሩ! አይ ቅንብቢት! አይ ጉሊት አይ ጋፈሮ! አይ አዲስ ከተማ! አይ ሐሙስ ገበያ! አይ ኮረማሽ! አይ ግምጃ ቤት) አይ ጆቢር ሜዳ አይ ሰንጋ… ፍንክርክር ውንክርክር ያለው ስልክ እንጨታችሁ ብቻ አይደለም፡፡ ገመናችሁፉ ጭምር ነው፡፡ ምንድነው ያናደደኝ? ሊስትሮው ጭኑ ላይ ያጋደመውን ጫማ ማሰሪያ አንስቶ በየቀዳዳው መክተት ጀምሯል፡፡“እ? ምን ልበላቸው?” ሲል ጠየቀኝ ለወሬው ትኩረት መስጠቴ አበረታትቶታል፡፡”ምንም””እንዴት?”አፈጠጥኩበት፤ እሱ ምን ያድርገኝ?”ብድር ይስጠን ያሉም አሉ፡፡””አባ ዲሪባጋ ይሄዱ፣ አራጣ በሊታውጋ””?”ልክ እንዳልሆንኩ ገባኝ።”የታለ ስልካቸው?”ከተጨበጠ ጭኑ ውስጥ እየፈለቀቀ ብዙ ብጥቅጣቂ ወረቀቶች አወጣ፡፡ እየገላለጠና በወግ እየዘረጋጋ ሰጠኝ፡፡ አብዛኞቹ ወረቀቶች ስልክ ቁጥር ብቻ ናቸው:: ስም ሆነ የሚፈልጉት አልተፃፈባቸውም። እያየሁ መለስኩለት”ምነው?”“ማነው? ምንድነው? አይታወቅም”

“አ-ሀ ያጤናቸው ጀመር።ድጋሚ የተጨበጠ ጭኑን ፈልቅቆ ሌሎች ኩርማን ወረቀቶች አወጣ። እየዝረጋጋ ሰጠኝ አንዳንዶቹ ብቻ ከስልክ ቁጥር ጋር ስማቸውን አክለዋል:: ስገላልጥ አንዲት ብጣሽ ላይ ያስደነገጠኝን ስም አየሁ፡፡ ቤባ-ንያ ይላል:: ባለማመን ወደ አይኖቼ አስጠጋሁ:: ቤባንያ!ኳ! ኳ! ኳ! ኳ! ኳ*እስኪ አንተ ደሞ” አመናጨኩት:: ቤባንያ ምን ፈልጋ? በኑሮ አሽቆልቁላ ወርዳ ግርድና አሮባት? ወይንስ ዕድሜዋ በመንዘላዘል አልፎ የሴትነት አፋፍ ላይ ሆና ሳትወድቅ በፊት ከሆነው ጋር ለመኖርና ለመውለድ ወንድ አሰኛት? ወይንስ በመወደዷ ዘመን ያሳየችኝ ቸልታ ቆይቶ ረመጥ ሆኖባት ለይቅርታ…ኳ ኳ ኳእስኪ አንተ ደሞ!!”ቁጥሮቹ በቢራቢሮ፣ ስሟ በሽልምልም የመስቀል ወፍ የተፃፉ ይመስል በፀጥታ ላረጋጋቸው ጣርኩ:: በአንድ ወቅት ይሄ ወረቀት እርሷ ዘንድ ነበር – ታድሎ!! በአንድ ሌላ ወቅት እነዚህ ቁጥሮችና ፊደሎች ቤባንያ ውስጥ በሙቀት የተሸረቡ እሷነቷ ነበሩ ይገርማል! ቁጥርና ፊደል ሆኖ ቤባንያ ውስጥ የመኖር እጣፈንታ እንዴት ያል ግሩም ዕድል ነው?ኳ! ኳ! ኳ!”እስኪ አንተ ደሞ!!”ሽኖን ከቤባንያ ጋር ሳስባት ከስምጧ በሚወጣ ብርሃን ተሽለምልማ፤ አበቦች፣ ቢራቢሮዎች፣ የመስቀል ወፎች፣ የቀይ እፉ ዬገላ ግንጣዮች፣ ወይን ጠጅ አሸኖች… ሞልተውባት አይንና ቀልብ ግታጠምድ ነው፡፡ ሸኖ ያለቤባንያስ? ብዙ የሰቀቀን ድምፆች ከትልነት

ወደ በራሪነት ተሸጋግረው ባገኙት ላይ ሁሉ ሲያርፉ፤ ማረፋቸው መዘግነን ሲሆን ነው፡፡የተጠረገ ጫማዬን ሳላይ ድፍን አስር ብር አውጥቼ ሰጥቼው መንገድ ጀመርኩ። “መልስ” የታማኝነት የሚል አልተከተለኝም:: ዘወር ብዬ አየሁት፣ ለተጨማሪ ሥራው፣ ተጨማሪ ጉርሻ እንደሰጠሁት ተቀብሎ የተቋጠረበት ቦታ ይፍነከነካል:: ሊስትሮው በዚያች ወረቀት ማስተላለፍ ውስጥ ምኔን ነካኝ? እኔስ ብር በሚባል ወረቀት መስጠት የትኛውን አካሉን አገኘሁት? ገንዘብ! ገንዘብ! ገንዘብ!……ከተራ የኢኮኖሚ አስተሳሰብ እንዳመለጠ፤ ያልገባን ገንዘብ! ተፈጥሯችንና ማሰቢያችን ከሆነ የቆየ _ ወረቀት:: ምሁራኖቹ “የዝውውር ማዕክል” ይሉታል፡፡ አይደለም! ምናልባት ‘የደም ዝውውር ማዕከል’ ይሆን ይሆናል። የእሴት መለኪያ” ይሉታል፡፡ አ-ይ-ደ-ለ-ም! ምናልባት የትንፋሽ መለኪያ’ ይሆናል። “የክምችት መሣሪያ፣ የክፍያ ማስፈፀሚያ፤ ዓለማቀፍ የልውውጥ መገልገያ’ ገንዘብ ይሄ ብቻ አይደለም:: ተፈጥሯችንን የተቀላቀለ፤ የምንሞትለትና የምንገልለት የስበት ህግ ሆኗል፡፡ማርክስ “በዚህ ዓለም ላይ ከገንዘብ ዕኩል ምትሀት የለም” ያለው ለዕውነታው ይቀርባል።ድንኳኑ ጋ ደርሼ ልገባ ስል ከአቦ ጎን አባ ዲሪባ ተቀምጠዋል፡፡ የአራጣ ልምድ _ ልውውጥ ፈልገው ይሆን? ባንካችን ከአራጣ አበዳሪዎች አባ ዲሪባን፤ ከጠንቋዮች አቦን ከያዘ ምን ቀረው?

Related Articles

ቤባንያ ገፅ ፲፪

“ቋ!ቋ!ቋ!ቋ!…" “ምን ሆንሽ አመቴ!" አንድ ጥግ ላይ ተጎዝጉዞላት የተኛች አሮጊት ናት፡፡ “ምን ሆንሽ?” “ጥለውኝ ሄዱ" ባለፈውም የሰጠችው ምክንያት ነው:: “ጅብ ሊያስበሉኝ እዚህ...

ቤባንያ ገፅ ፲፪

“ቋ!ቋ!ቋ!ቋ!..." “ምን ሆንሽ አመቴ!" አንድ ጥግ ላይ ተጎዝጉዞላት የተኛች አሮጊት ናት፡፡ “ምን ሆንሽ?”“ጥለውኝ ሄዱ" ባለፈውም የሰጠችው ምክንያት ነው:: “ጅብ ሊያስበሉኝ እዚህ...

ቤባንያ ገፅ ፲፩

በመጀመሪያ ኬኦስ ነበረ፣ የማይጨበጠውና ዉጥንቅጡ ኬኦስ የረጋቸውን ምድር(ጂኦን) ወለደ:: "እንዴት?" አይባል የሚያሰኘው የእኔ ከምንም ውስጥ መገኘት ነው፡፡ ሃይፒሪዮን ፀሐይን፣ ጨረቃንና...

Comments

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *