ኩራዙ በየቀን ብርሃን ተውጣ ስንጥር የመሰለ ጨረር ታግለበልባለች፡፡ ዝም ብዬ ቆምኩ፡
“ሃሎ ሚስተር ባንከር” አለኝ ድምፁ ብቻ ብቅ ብሎ ዝም አልኩት፡፡
“ለከተማህ መቅሰፍት ይዘህ መጣህ? አባ ዲሪባን ከነአራጣው በሺህ አባዝተህ ከተማው ላይ በተንክ ማለት ነው::” ብቅ አለ፡፡ ዝም አልኩት፡፡
“ባንከርን በትክክል የገለፀው አሜሪካዊው ደራሲ ማርክ ትዌይን ነው፡፡ ‘ባንከር ፀሐይ ባለጊዜ ያዋሰህን ጃንጥላ ዝናብ ጠብ ሲል ጠብቆ እንድትመልስለት የሚጠይቅ ሰው ነው አለ፡፡ አካካካካካ! A Banker is a fellow ከእንጨት በርሜሉ እየተጎተተ ወጣ who lends you his umbrella when the sun is shining ከወገቡ ጋር የተገመደ የተገመደ አሮጌ ብርድልብስ አብሮት እየተጎተተ ወጣ። but wants it back the minute it begins to rain” ከወገቡ በላይ ራቁቱን ነው:: የደረት አጥንቱ እንዳልተቃኘ የክራር ክር ረግቦ ይታያል፡፡
ምን ልለው ነበር የመጣሁት?
ክብርዎን ስነካ የግድዎን ይፋለሙኛል” በሚል የስድብ መዓት ያወርድባቸዋል፡፡ዝም ይሉታል፡፡የሰድቡን አይነት በመለወጥ እጅግ ክብረ ነክ ወደሆነ ደረጃ ያሳድገዋል።አሁም ዝም ይሉታል:: በዚህ ሁኔታቸው ደቀመዝሙሮቻቸው ሁሉ ይበሳጫሉ፡፡ያ የመንደር አውደልዳይ በስድቡ ተነክተው ሊፋለሙት እንዳልፈቀዱ ባየ ጊዜ የመንደሩን ሰው ሰብስቦ በኩራት ወደ መኖሪያው ይመለሳል፡፡ሊቁ ደቀመዝሙሮቻቸውን ወደ ማስተማሩ ሊያመሩ ሲሉ ፈቃዳውን ነፈጓቸው።“ይሄ የመንደር አውደልዳይ የእርስዎን ያህል የሰይፍ ችሎታ እንደሌለው እየታወቀ ሲሰድብዎትና ሲያዋርድዎት ለምን ዝም እንዳሉ ይንገሩን” ይላሉ ደቀ መዝሙሮቹ::“አንድ ሰው ስጦታ ይዞላችሁ መጣ እንበል” አሉ ሊቁ”እሺ”“ያንን ስጦታ ባትቀበሉ ስጦታው የማን ይሆናል?” ሲሉ ጠየቁ።”የአምጪው”“ጥሩ፣ ስድብም እንደዚያው ነው፤ካልተቀበላችሁት ለተሳዳቢው ተመላሽ ይሆናል::” ደስ የሚል ሣቅ አሰማኝና እየቀረበኝከእኛ የተገኘ ዕውቀት ደሞ እነሆ” አጎነበሰ፣ ብርድ ልብሱን ጠቅልሎ ከወገቡ ጋር የተቋጠረውን ፈትቶ ወደ በርሜሉ ውስጥ ወረወረ።“እስኪ ልነሳና እንዝርቴን ላስላው፣ ምን ያቦዝነዋል ፈትሎ `ሚያድር ሰው::” ፈገግ ብሎ እያየኝ።“ለእንደዚህ ያለ ማህበረሰብ፤ ገመናውን በመሸፋፈን የሺህ ዓመታት ልምድ ላለው ህዝብ ስድብህን ወደ ኋላ ደብቆ አክብሮት በማሳየት የሚያገለማ ጥንጣን ህብረተሰብ ፈትሎ ሚያድር ያስፈልገዋል፡፡ የውርደት መሠረት ላይ ኩራትን ለገነባ ሰው ከስድብ ሌላ መፍትሔ ስራይ አለው?… የለውም!! _ አንተ ያላፈርከው ለምንድነው? የመሸፋፈን ባህላችን ስላልገላለጠህ ነው? ከዚህ ጊዜ በኋላ የነበርክበትን ህይወት ሳትፀየፍ እንዴት እንዳለ ተቀላቀልከው? ከየት መጣሁ ብለህ እንዴት አትጠይቅም?…”መንገድ ጀመርኩ…“እንካ! ይቺ ኩራዝ ያንተን በብርሃን ውስጥ የተደበቀ የጨለመ ህይወት ማፈላለጊያ ናት!…””ሠቆቃወ ሆሴዕ “የሚል ቃል ውስጤ ተደጋገመ:: የሆሴዕ ሠቆቃ፣ ሠቆቃወ ሆሴዕ… የመጥፎ ዘመን መገሰጪያ፡፡ ሲሰድበኝ ለምን አልጠላሁትም? ግን ሰደበኝ? እራሴ ያዳፈንኩት፣ ግን ላዳፍነው የማይገባ እውነቴን አስስ አለኝ፡፡ ይሄ ስድብ ነው?
ክፍል 6ለማና አሜልክቱይሄ ስድብ ነው? ካልሆነ ለምን ከነከነኝ?እኔ ከማዳፈኔ ባሻገር ስለምን እናት ነኝ፤ አባት ነኝ የሚል ሳይመጣ ቀረ? እሺ የወለዱኝ አይኑሩ፤ እንዴት የእናት ዘመድ ነኝ፤ የአባት ዘመድ ነኝ የሚል ሳያፈላልጉኝ ቀሩ?ከሸኖ ሰማይና ምድር ሩካቤ ይሆን የተወለድኩት? የህላዌ ደጃፍ ላይ ወረፋዬን ስድሬ ቆሜ ከቲታንስ፣ ከክሮነስ፣ ከሳተርን፣ ከዚየስ፣ ከጁፒተር፣ ከኦሽን፣ ከጠሚስ፣ ከቲቲየስ፣ ከሐይፐሪየን… ኋላ በሰማይና በምድር የእርጅና ዘመን፣ ከደካማ ወገባቸው ተፈለቀቅሁ?ታድያ ለምን….. ?…መወለድን ተነፍጎ የሚፈጠር አለ? መወለድ ሰበብ ሆኖ? ያልተረጋገጠውን የመወለድ ቅጥ አጥቶ፣ የተገነጠለበትን የህይወት ቅርንጫፍ ተጭበርብሮ፣ ከዚህ ማን፣ ምን ያተርፋል?እንደ አፈ ታሪኩ ከሰማይና ምድር ብቻ ሳይሆን ከውቂያኖስ አረፋ፣ ከተቀደሰች ድንግል ላም፣ ከብርሃንና ጨለማ፣ ከፀሐይ… የተወለዱ እንግዳ አማልክት ትርክታቸው አለ፡፡
0 Comments