ቤባንያ ገፅ ፲፪

January 1, 2024

“ቋ!ቋ!ቋ!ቋ!…” “ምን ሆንሽ አመቴ!” አንድ ጥግ ላይ ተጎዝጉዞላት የተኛች አሮጊት ናት፡፡ “ምን ሆንሽ?”

“ጥለውኝ ሄዱ” ባለፈውም የሰጠችው ምክንያት ነው:: “ጅብ ሊያስበሉኝ እዚህ ጥለውኝ ሄዱ”

አባባን በሞግዚትነት ያሳደገች ባሪያ ነች፡፡ ታዲያ አባባ ስለሴትዮዋ ሲናገሩ እንባቸው የተጨናበሰ አይኖቻቸው ላይ ቸፈፍ ብሎ ነበር።

የድሮ ሰው ባሪያን እንደ አህያ፣ እንደፈረስ ሰርቶ ከጨረሰ በኋላ ወስዶ ሩቅ ቦታ ዛፍ ሥር አስቀምጧቸው ይመጣል:: ጅብ ነው የሚበላቸው፡፡ ይሄ ነገር ‘እምዬ’ ላይ ተቀርጾባት ቀርቷል፡፡ አይኗ ሲጠፋና መጃጃት ስትጀምር ያ ፍርሃት ይከባታል፡፡ ቁ! ቁ! ትላለች፡፡ ቁ! ቁ ታ ያስጥላት ይመስል፡፡

“እንዴ? እንዴ? እንዴ? አመቴን እዚህ የጣላት ማነው? በይ ተነሽ ወደቤታችን እንሂድ” አለች ጠና ያለችው ሴት፡፡

አመቴ በዳበሳ እጇን ሰጠች፡፡ እንደ ሆሴዕ ጨርቋ ብብቷ ውስጥ ገብቶ ደረቷ ተራቁቷል፡፡

“ጅብ ሊያስበሉኝ! ጅብ ሊያስበሉኝ!’ ትላለች።

“ጅብ ሊያስበሏት!”

ከሴትዮዋ ጋር ከቤት ወጥተው ግቢው ውስጥ ጥቂት እንደተጓዙ

“እንደምን አመሻችሁ!” ሴትዮዋ “እንደምን አመሻችሁ?” ፀጥ ብለው ሥራቸውን ሲያከናውኑ የነበሩት፡፡

“አመቴን ዛፍ ስር አግኝቻት! ጅብ ሊያስበሉብን። ይዣት መጣኋ“እንኳን አመጣሽልን፤ ጎሽ! ጎሽ! ግቡ ወደቤት!”“ሊያስበሉኝ! ጅብኮ ሊያስበሉኝ አመቴ በእርጅና የተሳሰረ እግሯን በግድ እየጎተተች ወደ ቤት ገባች፡፡የሰው ልጅ ከአጥፊዎቹ ጥቃት እራሱን ነፃ ከማድረጉ ያተረፈው ይሄንን የተንዛዛ የፍርሃትና የድራማ ህይወት ብቻ ነው ስል አሰብኩ:: ወደ መቀመጫዬ ስመለስ ቆሎው ተደፋፍቶ ዶሮዎች በትብብር ሲለቅሙት ደረስኩ፡፡ የማይበሉ ዶሮዎች የሚበሉትአይቆጭ ይሆን?አመቴ ከጭንቅላቴ አልወጣ አለች፡፡ማኅበረሰቡ ለጃጁት ያዘጋጀው ትርኢት እና ትወና እንዳለ ሁሉ፤ ለህፃናቱም፤ ለወጣቶቹም፣ ለጎረምሶችና ለጎልማሶች በየደረጃውብቅ የሚያደርገው ቅጂ ጥበብ አለው:: ለእኔ የሚያስፈልገውን ትዕይንት እነዚያ ሽማግሎች እንደ አመቴ እያጃጃሉ መልሱን እራሴ እንድፈልገው አድርገውኛል።ቤባንያ! ቤባንያ! ቤባንያ!እሷን አልመቷት ይሆን? እሷም እንደ እኔ አይኗን እየቃኘች ይሆን የምታየው?….. የቤባንያ ወንድሞች ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ደብድበውኛል። የመጀመሪያ ቀን ሹክ ባይ ጠቁሟቸው ስንጋቦካ ወንዝ መጡ፡፡ ዳር ቁጭ ብለን የውኃውን አወራረድ ስንመለከት ድንገት ከጭጋግ ውስጥ በየአቅጣጫው ከተፍ! ከተፍ! አሉ። ቀኑ የቁርጥ ስለነበር በአይኔ ተሰናበትኳት፡፡ ጨከነብኝ።ቤባንያ ስትጮህ ይሰማኛል። አንዴ እንኳ ስንዝሬ አንዱ ላይ እጄን ሳላሳርፍ በቤባንያ ታስሬአለሁና ያለምንም መንፈራገጥ የተተመነልኝን ዱላ ቻልኩ:: በመጨረሻ ስደክም አንስተው ወደ ሠማይ ወረወሩኝ:: መንሳፈፌ የህልም መንሳፈፍ ሆኖልኝ ዥው ብዬ በአየር ስሄድ ትዝ ይለኛል። ለካ የወረወሩኝ ወደሰንጋቦካ ወንዝ ኖሯል፡፡ እራሴን ከሳትኩበት ስነቃ ገበሬዎች ቤት ነኝ፡፡ የገበሬ ልብስ ለብሼ፣ የገበሬ መደብ ላይ ነት ተነጥፎልኝ ተኝቻለሁ:: ገርም ገብርኤል፡ ከበደ ሚካኤል የተወለዱበት፡፡ አሁንም ከእነሱ እጅ አልወጣሁም፡፡ የቤባንያ አባት አጎትየው የተወለዱበት፤ የሥጋ ዝምድና የተጠናከረበት:: ያገኙኝ ገበሬዎች የተጎሳቆሉ ፈረንጆች ናቸው:: ስለቤባንያ አንድም ነገር ሳልተነፍስ ከረምኩ። ምን ያህልእንደቆየሁ አላውቅም። ያገገምኩ ዕለት ከትንሽ ልጅ ጋር የሁለትሰዓት መንገድ ተጉዤ ሸኖ ደረስኩ፡፡ ቀጥታ ወደ ቤባንያ ቤት፡፡“ቤባንያ! ቤባንያ! ቤባንያ!”ፀጥ አለ ቤታቸው፡፡ ለካ የቤባንያ ወንድሞ ባልተረጋገጠ ገዳይነት ተጠርጥረው ሳምንት ሙሉ በስጋት ላይ ኖረዋል።“ቤባንያ! ቤባንያ!…”“በህግ አምላክ!…” ያሉት አንድ አሮጌ ፈረንጅ ነበሩ። “እባክህሂድልን!“ሳላያት አልሄድም! ገድላችሁ ቀብራችኋታል” አልኩ፡፡ ግራ በመጋባት ትክ ብለው አዩኝ። ጫ ብሎ ቤቱ የተደበቀ ጎረምሳ ሁሉ በመስኮት ብቅ እያለ ማየት ጀመረ፡አንዱ “አንተ ጅል በከንቱ ህይወትህን ሳታጣ ሂድ!” ከወንዱሞችዋ አንዱ “አልሄድም! ቤባንያን ገድላችሁ ጓሮ ቀብራችኋታል! ሳላያት አልሄድም” ጅስም ጎድሎኛል፡፡ መተንፈስ እንኳ እየተገዳደረኝ ነው፡፡አባትየው ገብተው ይዘዋት ወጡ! “ቤባንያ እወድሻለሁ”

Related Articles

ቤባንያ ገፅ ፲፩

በመጀመሪያ ኬኦስ ነበረ፣ የማይጨበጠውና ዉጥንቅጡ ኬኦስ የረጋቸውን ምድር(ጂኦን) ወለደ:: "እንዴት?" አይባል የሚያሰኘው የእኔ ከምንም ውስጥ መገኘት ነው፡፡ ሃይፒሪዮን ፀሐይን፣ ጨረቃንና...

ቤባንያ ገፅ ፲

ኩራዙ በየቀን ብርሃን ተውጣ ስንጥር የመሰለ ጨረር ታግለበልባለች፡፡ ዝም ብዬ ቆምኩ፡ “ሃሎ ሚስተር ባንከር" አለኝ ድምፁ ብቻ ብቅ ብሎ ዝም አልኩት፡፡ "ለከተማህ መቅሰፍት ይዘህ መጣህ?...

ቤባንያ ገፅ ፱

"እኔና አንቺ?"ጅል' ሳቅ ፈለቀች፣ አሳዘንኳት፤ አፌ ላይ ሳመችኝ። ምንድነው ተአምሩ? ከንፈሬና ልቤን የሚያገናኝ ምን መስመር ተዘርግቷል? መቼ ይሆን ዳግም የምትስመኝ?“ኧረ ሸኖዎች። ብዙ...

Comments

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *