ቤባንያ ገፅ ፲፩

December 28, 2023

በመጀመሪያ ኬኦስ ነበረ፣ የማይጨበጠውና ዉጥንቅጡ ኬኦስ የረጋቸውን ምድር(ጂኦን) ወለደ:: “እንዴት?” አይባል የሚያሰኘው የእኔ ከምንም ውስጥ መገኘት ነው፡፡ ሃይፒሪዮን ፀሐይን፣ ጨረቃንና መንጋትን ወለደ። ፀሐይ፣ ጨረቃና ንጋት የሚወለዱ ነገሮች ናቸው? ይሄ ሁሉ ተአምር መገኛ ምንጭን ካለማወቅ ከእኔ ታሪክ ተአምርነት አይበልጥም::

የሸኖ ህዝብ ያንን የእኔን ተአምር ምናልባትም አይቶና ሰምቶ እንደምን ያየና ያዳመጠ አለመምሰል ቻለበት? ተአምርን በሆድ መያዝ አያፋፍምም? ማድመጥስ መውጪያ ጠብቦት ምጥ አያከፋም? እና የሽኖ ሰው ፊት ላይ እኮ ይሄ ጭንቅ አይነበብም:: እውነት! ከየት መጣሁ ብዬ የማንን ፊት ልጠይቅ? አፍራሙን የሸኖ ሰው ፊት ያለሐፍረት በዘበዝኩ፡ ዓይን ላወጣው ግትርትር እይታዬ እንኳን መልሱ አንገቱን ቀልሶ ማለፍ ብቻ ነበር።

ቤባንያን አፍቅሬ ድፍረቱን ሳበዛውና ወንድሞቿ ሊገድሉኝ ሲደርሱ፣ አንዳንድ ሽማግሌዎች ጣልቃ ገብተው እኔን ለማብረድ የሞከሩበት መንገድ ዛሬ ከተብከነከንኩበት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበረው ነው:: ከሽማግሌዎች አንዱ

“እኛ ሽማግሌዎች ነን፤ በቤባንያ ወገን አባቷን አነጋግረን የደረስንበት ስምምነት አለ:: እስኪ ደግሞ በአንተ ወገን የምናናግረው ሽማግሌ ሰው ማነው?”

“አቦ አለ” አልኩ:: የቤባንያ ወንድሞች ሲደበድቡኝ የተጎዳ አንድ አይኔን መግለፅ ተስኖኝ እንደጨፈንኩ።

“አቦ ማነው?”

“ኮርማ ብሩ” በተጨናበሰ ሁኔታ የሳቁ መስለኝ፡፡

“አ-ይ የልጅ ነገር! በቤባንያ በኩልኮ ያናገርነው አባቷን ነው። የአንተም አባትህ መሆን አለባቸው”

ዝም አልኩ:: ያላወኩት አካሌን ያመኛል። ምኔን ተመትቼ ነዉ?

“ከኮርማ ብሩ በፊት ያሳድግህ የነበረው? እ… ማነው ልጄ?… ሌላኛው ሽማግሌ“ጋሽ ይማም” አልኩ ድንገት ናፍቆቱ ውርርር… እያደረገኝ:: በአይኔ ምክንያት ሚዛን ተዛብቶብኛል። ከይማም በፊትስ?..” እየተፈራረቁ ሊያደክሙኝ የፈለጉ አስመሰለባቸው:: ሽማግሌዎቹ እየተረዳዱ ሊከተሉኝ ያሰቡበት ጨለማ ሽንቁር መስሎ ከሩቅ ታየኝ:: አፈገፈኩ:: ግን ጨርሶ ተስፋ አልቆረጥኩም:: አንድ አዛውንት በአባትነት የሚቆምልኝ ባገኝ ዕለቱን ቤባንያን ወደ ቤቴ ይዤ የምገባ ያህል ተሰምቶኛል፡፡ወደ አስታርቂኝ ማሪያም አፀድ የለመደውን አነበነበ፡፡ ከየት አመጣሁት? እንጃ!ወይቤልዋ በእግዝእትነ ማሪያም ሰላምለኪ አብፅዕት ወኃሪቱ ለእግዚአብሔር።(እመቤታችንንም ለእግዚአብሔር እናትነት የተመረጥሽ ንኡድ ክብርት ሆይ ፍቅር ይገባሻል።) ወደ ውስጥ ዘለቅሁ፡፡በጮርቃ አይኖቻቸው በፍቅር የሚመለከቱኝ አዛውንት አልነበሩም:: እስኪመጡ መጠበቅ አልቻልኩም፡፡ ቤታቸውን አሳይተውኝ ስለነበር ወደዚያው አመራሁ። ጋፈሮ ሩቅ አይደለም፡፡ ቤታቸው ባለብዙ ቤተሰብ ነው:: ምድረ ግቢው ሠፊ ቢሆንም ከዋናው ቤት ውጭ ጊዜያዊ ከለላ ይበዛዋል።”በፊት የምጠራው “አባባ ውለታ ቢሱ’ እየተባልኩ ነበር፡፡” ብለውኛል በፊት፡፡“ለምን? ማን ያወጣሎት ነው? የትምህርት ቤት ስምዎት ነው?” ጥያቄ አከታተልኩ።

Related Articles

ቤባንያ ገፅ ፰

“አውርድ አንተ ጅል ትላለች ብዬ ጠበኩ ዝም አለች የእነሱን ሠፈር ርቀን ሄደናል፡፡ የጉልት ገበያ በአመሻሽ ግብይት እንደመሞቅ ብላለች፡፡ የዕለት ፍጆታዎችን ለመሸጥ ቁጢጥ ቁጢጥ ያሉ ሴቶች...

ቤባንያ ገፅ ፯

ክፍል 4 ለማና ወዳጄ ልቤ ቤባንያ የክልስ መልክ አላት፡፡ ገና ዘጠነኛን እንዳለፍን እኛ ክፍል ቁጭ ብላ አገኘኋት። ልቤ “ባትጋሩኝ አለ ተሽቀዳድሞ:: እንደአልማዝ' እንደዕንቁ፣ እንደ...

ቤባንያ ገፅ ፮

“ታዲያ ምን ሆኖ ነው? እቃጠለኝኮ ተቃጠልኩ ውሃ የለም?” እኔ እቀጥላለሁ፡፡ "ከገንዘብ ይልቅ የዕታ ለዕቃ ልውውጥ እንደሽኖ ላሉ ነባር ከተሞች ውጤታማነቱ ተረጋግጧል፡፡ (ማነው...

Comments

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *