ቤባንያ ገፅ ፭

December 19, 2023

ክፍል 3

hማና ሰንክሳሮቹሽኖ አልጋ ይዤ ለማደር ብመኝም የሚያረካ መኝታ አላገኘሁምና ወደ ኮርማ ብሩ ግቢ አመራሁ። አቦ አርጅቷል፡፡ የተቀመጠበት ጉዝጓዝ ድረስ ሄጄ ሳምኩት፡፡ ግንባሬ ላይ ምራቁን እያርከፈከፈ መረቀኝ። ከኔ አልፎ በዙሪያው ያሉትን ሁሉ መረቀ።“ፈያ ኢሳኒ ሀኬት” (ጤና ይስጣችሁ!)“ሆራ ብላ” በልፅጉ“ፈያ ሀሲከኑ ወደታመመች ሴት ዞሮ (ጤና ይስጥሽ)“ለፍ ነጋ ሀኑቶልቹ” (ምድርን ሠላም ያድርግልን)“ዋሪ ነጋ!” (ሠፈር ደህና ይሁን!)“ረራ ነጋ!” (መንደሩን ደህና ያድርግ)ከምረቃ በኋላ ወደተዘጋጀልኝ ክፍል ገባሁ:: መሬት ቢሆንም ተደልድሎ ተነጥፎልኛል:: የልብስ ሻንጣዬን አስቀምጬ አረፍ እንዳልኩ ጠና ያለች ሴት በእሽኩርሚሚት በር ከፍታ እጅ ማስታጠቢያ አቀረበችልኝ። ዛራ እህል መቅመሴ ትዝ አላለኝም። ውኃው እጄ ላይ ሲያርፍ ለብ ያለ ሙቀት ወደእኔ አስተላለፈ፡፡ፍጥጥ ያለው የእንጀራ ዓይን ውስጥ ፍጥጥ ያለ አተር ክክ የተሰገሰገበት ማዕድ ቀረበልኝ፡፡ ሲያዩት ባያምርም! ሲበሉት ይጥማል።እጅ አስታጣቢዬ ስትመጣ፣ እስክሪፕቶና ወረቀት ፈልጊልኝ አስቲ” አልኳት አስታጥባት እንደወጣች፦“ቤላ፣ ቤላ… ለእንግዳ ወረቀት ስጪ’ መጣፊያም ይፈልጋል አለች። ከጥቂት ጥበቃ በኋላ አንድ ቀጭን፤ ቀይ እጅ ተንዃኑ ወረቀትና እስክሪፕቶ ወደውስጥ ጣለ፡፡ ያስገረመኝን የቤላ ነገር ትቺ ነገ ለሚመረቀው ቅርንጫፍ ባንክ የሚደረገውን ንግግር ወደ ማምሰልሰል ተሸጋገርኩ፡፡ነገ ለምረቃው ዋና እንግዳ ሆኖ የሚመጣው ማን ይሆን? ሪቫኑን የሚቆርጠው ከማን ጋር ነው? ስማቸው የንግግሬ መግቢያ ላይ ሳይጠቀስ የማይታለፍ ይኖር ይሆን?…እነዚህን ሁሉ ነገሮች ትቼ ዋነኛ ንግግሬ የሚያተኩርበትን ብቻ ማምሰልሰል አስቀደምኩ……ሸኖ በዚህ ግዜ አንድ ብቸኛ ቅርንጫፍ ባንክ መመስረቱ አካባቢው ያለውን ሀብትና የንግድ ልውውጥ ካለመገንዘብ የተፈፀመ ስህተት እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌለ መጥቀስ (ያጣላኝ ይሆን?)ሽኖ በቅቤ’ በማር፤ በቁም ከብትና በተለያዩ እህሎ‐ች የበለፀገች በመሆኗ የንግድ ልውውጧ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ (ጥናት ይኖር ይሆን?) ከመሆኑም በላይ፣ አዲስ አበባና ሌሎች በየደረጃው ያሉ ከተሞች የንግድ ልውውጡ ተሳታፊዎች ናቸው።ስለዚህ ሽኖ ይሄንን የንግድ ልውውጥ የሚያሳልጥላት የባንክ አገልግሎት ያስፈልጋታል:: በመሆኑም የእኛ ባንክ ቀዳሚን ተቆርቋሪነት በመውሰድ የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ ከፍቷል፡

ሽኖዎች “የኔ” ብለው ተቀብለው የባንካችንን ስራ የተቀላጠፈር የተስፋፋ እንዲሆን እንደሚተባበሩ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ:: (የፃፍኩት ረቂቅ ንግግር አልጣመኝም፡፡) * * * *የሸኖ ጭጋግ መግፈፉ እንደአንድ ተአምር ሆኖ ተቆጠረልኝ:: ዳመናው ብቻ ከማስጫ ጋር ታብቶ በነፋስ እንደሚመናቀር ጨርቅ ቦታውን ሳይለቅ ይንቀሳቀሳል።ግዙፍ ድንኳን ተጥሏል:: ማሽብረቂያ ፊኛዎቹ የባንኩን የአርማ ቀለም እንዲከተሉ ሆነው ተንጠልጥለዋል:: እንግዳ ተቀባዮቹ የማሸብረቂያ ፊኛዎቹን ቀለሞች የተከተለ የጥበብ ልብስ አድርገዋል::ጫማዬን እንዳላስጠረኩ ያስተዋልኩት ወደ ውስጥ ከዘለቅሁ በኋላ ነበር። ለዋነኞቹ እንግዶች የተዘጋጀው መቀመጫ ላይ አቦ ተኮፍሶ ሳየው ድንጋጤ ልቤን ተረተረው:: ግራ ተጋብቼ እንደቆምኩ የፊኞቹ መንትያ የመስለች ጥበብ ለባሽ እየመራች ወስዳ በአቦ መደዳ ጥቂት ፈቀቅ ያለ ቦታ ላይ አስቀምጣኝ ተመለሰች።ሁሉም _ ነገር _ አስጠላኝ፡፡ አይኔን፣ እጄን፣ እግሬን… ማስቀመጫ ቦታ አጣሁ፡፡ እነዚህ ሁሉ የሰውነት ክፍሎች ትር የሚሆኑበት ጊዜ አለ ማለት ነው?አንድ ከብላላ ስው መጥቶ አጠገቤ ተቀመጠና _ ለጆሮዬ አዘንብሎ፤ “ስጠኝ በግዱ እባላለሁ” አለኝ። ሳቄ መጣ፤ እንደምንምን ተቆጣጥሬ“እሺ?” አልኩት፡፡hDevision manager ቢሮ ነው የመጣሁት።”እሺ””Branch Expansion ውስጥ ስለሆንኩ የዚህ ቅርንጫፍ ቤት ማፈላለግ ሆነ መከራየት! ከዚያም አሳድሶ እንዲመረቅ ማድረጉ ሁሉ በእኔ ሥር የተከናወነ ነው።””ማድነት ይገባኝ ይሆን? ወይም ተነስቼ በሁለት እጄ መጨበጥ…”ስለዚህ የማስመረቅ ሥነ-ሥርዓቱን የምመራው እኔ ነኝ ሪሻን የማስቆረጡንና ለንግግር መጋበዙን እኔ እወስዳለሁ::”ወረቀቱን ከውስጥ ኪሴ አውጥቼ የሚመጣው እንግዳ ማነው; ማለቴ ሪቫኑን የሚቆርጠው?…ከአዲስ አበባ ልከናል እያሉ ነው:: አላወቅንም።” ማን እንደሆነ“ስሙ ቢታወቅወንበር አልበቃ ብሎት እኔ ላይ እየተደረበ”ለምን?””ንግግሩን ሳደርግ…”እኔ ስለሱ አንቄ የያዝኩት ሳቅ እሱጋ ሲደርስ ስለእኔ አልያዘውም፤ አመለጠው::ጊዜ የለም፣ እንግዳው ይመጣሉ፣ ሪቫኑን እዛች ጋ በሁለት ቋሚ ላይ እናስራለን፣ ይቆርጣሉ፤ ንግግር ካደረጉ፣ ጥሩ1 የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ማብቂያ ይሆናል”እግሬን ማስቀመጫ ቦታ ያጣሁለት ጫማዬ ስላልተጠ ነው:: እጄና አይኔስ? ለምን ማስቀመጫ ቦታ አጣሁላቸው?”እንግዳው የት ደርሰዋል?”

እንጂ! ቢያንስ አንድ ሰአት ግን ያስፈልጋቸዋል ሰውነቱን ከሰውነቱ ጥላ ፈልቅቄ አወጣሁ:: ቅልል ያለኝ መሰለኝ፡፡ ግን እንዴት ግግር አላደርግም? ቦታው ለእኔ እንጂ ለነሱ ምንማቸው ነው? እንዴት…ጫማዬን ላስጠርግ ወደ ጉልት አቅጣጫ ሄድኩ:: ኦቦ አሳዘነኝ፡፡ ምናልባት እኔ ልጁ በንግግር ስቀናጣና፣ ሲያሸረግዱልኝ ለማየት ይሆናል የመጣው:: አበቃ! ማለት አሰኘኝ። ለመሆኑ ሸኖ ባንክ ያስፈልጋታል?… ሁሉንም ነገር ማፍረስ አሰኘኝ:: መፍትሔው ጫማ ማስጠረግ ይመስል ፈጠንኩ።ሽኖ እቃ-ብእታ መለዋወጥ መች አንሷት? ቤታችን የተትረፈረፈውን ይዘን አንዲት መገናኛ ቦታ ላይ መቆም፣ ሌላው ቤቱ የተትረፈረፈ፣ ግን እኛ ዘንድ የሌለ ይዞ ሲመጣ መለዋወጥ። በቃ! ገንዘብ፤ ባንክ ለሸኖ ምን ያደርግላታል?ይሔንን ሐሳብ የሚያንፀባርቅ ንግግር እዚያ የምረቃ ድንኳን ውስጥ ማቅረብ፤ መጀመሪያ ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ የሰጠውን ምክር መጥቀስ። “ግንዘብ የክፋት ሁሉ ሥር ነው፤ አንተ /ጢሞቲዎስ ግን የእግዚ አብሔር ሰው ሆይ ከዚህ ሽሽ”ታላላቆቹ ባንከሮች አፋቸውን ከፍተው ዝም!የሰው ህይወት በገንዘብ አይድንምና (ጢሞቲዎስ ሆይ)ተጠበቅ::”እርስ በእርስ ይተያያሉ፡፡”አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለመውደድ ይሁን”“ማነው?” (መቼም አያውቀኝም)“ዋናው መስሪያ ቤት relief manager ነበር። ለዚህ ቅርንጫፍ manager ሆኖ የተመደበ ነው::”

Related Articles

ቤባንያ ገፅ ፲

ኩራዙ በየቀን ብርሃን ተውጣ ስንጥር የመሰለ ጨረር ታግለበልባለች፡፡ ዝም ብዬ ቆምኩ፡ “ሃሎ ሚስተር ባንከር" አለኝ ድምፁ ብቻ ብቅ ብሎ ዝም አልኩት፡፡ "ለከተማህ መቅሰፍት ይዘህ መጣህ?...

ቤባንያ ገፅ ፱

"እኔና አንቺ?"ጅል' ሳቅ ፈለቀች፣ አሳዘንኳት፤ አፌ ላይ ሳመችኝ። ምንድነው ተአምሩ? ከንፈሬና ልቤን የሚያገናኝ ምን መስመር ተዘርግቷል? መቼ ይሆን ዳግም የምትስመኝ?“ኧረ ሸኖዎች። ብዙ...

ቤባንያ ገፅ ፰

“አውርድ አንተ ጅል ትላለች ብዬ ጠበኩ ዝም አለች የእነሱን ሠፈር ርቀን ሄደናል፡፡ የጉልት ገበያ በአመሻሽ ግብይት እንደመሞቅ ብላለች፡፡ የዕለት ፍጆታዎችን ለመሸጥ ቁጢጥ ቁጢጥ ያሉ ሴቶች...

Comments

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *